ኢሳይያስ 43:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዓይኔ ፊት የከበርህና የተመሰገንህ ነህና፥ እኔም ወድጄሃለሁና ስለዚህ ሰዎችን ለአንተ፥ አሕዛብንም ለነፍስህ እሰጣለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለዐይኔ ብርቅና ክቡርም ስለ ሆንህ፣ እኔም ስለምወድድህ፣ ሰዎችን በአንተ ምትክ፣ ሕዝቦችንም በሕይወትህ ፈንታ እሰጣለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ በእኔ ፊት የተወደዳችሁ ናችሁ፤ ስለምወዳችሁ ሕይወታችሁን ለማዳን ሕዝቦችንና መንግሥታችን አሳልፌ እሰጣለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በፊቴ የከበርህና የተመሰገንህ ነህና፥ እኔም ወድጄሃለሁና ስለዚህ ብዙ ሰዎችን ለአንተ ቤዛ፥ አለቆችንም ለራስህ እሰጣለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዓይኔ ፊት የከበርህና የተመሰገንህ ነህና፥ እኔም ወድጄሃለሁና ስለዚህ ሰዎችን ለአንተ አሕዛብንም ለነፍስህ እሰጣለሁ። |
አሁንም ከማኅፀን ጀምሮ በሠራኝ በጌታ ዐይን ከብሬአለሁና፥ አምላኬም ጉልበት ሆኖኛልና ያዕቆብን ወደ እርሱ እንድመልስ እስራኤልንም ወደ እርሱ እንድሰበስብ አገልጋዩ አድርጎኝ ጌታ እንዲህ ይላል።
ወድጃችኋለሁ ይላል ጌታ፤ እናንተ ግን፦ “እንዴት ወደድከን?” ትላላችሁ። ዔሳው የያዕቆብ ወንድም አልነበረምን? ይላል ጌታ። ሆኖም ያዕቆብን ወደድኩት።
ይህም እኔ በእነርሱ አንተም በእኔ ስትሆን፥ በፍጹም አንድ እንዲሆኑ፥ እንዲሁም አንተ እንደ ላክኸኝና በወደድኸኝም መጠን እነርሱን እንደ ወደድሃቸው ዓለም እንዲያውቅ ነው።
ምክንያቱም አንተ ለአምላክህ ለጌታ ቅዱስ ሕዝብ ነህ፤ ለራሱ የተለየ ሕዝብ እንድትሆንለት ጌታ በምድር ላይ ከሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ አንተን መርጦሃል።
መድኃኒታችንም ከኃጢአት ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።
በዚህም በእሳት ምንም ቢፈተን ከሚጠፋው ወርቅ ይልቅ አብልጦ የሚከብር የተፈተነ እምነታችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ፥ ለምስጋናና ለክብር ለውዳሴም ይገኝ ዘንድ ነው።
እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን አስደናቂ ሥራ እንድታውጁ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ እግዚአብሔር ለራሱ ያደረጋችሁ ቅዱስ ሕዝብ ናችሁ።
እነሆ አይሁድ ሳይሆኑ ‘አይሁድ ነን’ ከሚሉ ነገር ግን ከሚዋሹ ከሰይጣን ማኅበር አንዳንዶችን እሰጥሃለሁ፤ እነሆ መጥተው በእግሮችህ ፊት ይሰግዱ ዘንድ እኔም እንደ ወደድሁህ ያውቁ ዘንድ አደርጋቸዋለሁ።