La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢሳይያስ 37:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እነሆ፥ በላዩ መንፈስን እሰድዳለሁ፥ ወሬም ይሰማል፥ ወደ ምድሩም ይመለሳል፤ በምድሩም ላይ በሰይፍ እንዲወድቅ አደርጋለሁ በሉት’ ” አላቸው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እነሆ፤ በላዩ መንፈስን እሰድዳለሁ፤ ወሬም ሰምቶ ወደ አገሩ ይመለሳል፤ በገዛ አገሩም በሰይፍ እንዲወድቅ አደርጋለሁ።’ ”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በሀገሩ ስላለ ጉዳይ በሹክሹክታ ወሬ እንዲሸበርና ወደ ሀገሩ ተመልሶ በሰይፍ እንዲገደል አደርገዋለሁ።”

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እነሆ፥ መን​ፈ​ስን በላዩ እሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ ወሬ​ንም ይሰ​ማል፤ ወደ ምድ​ሩም ይመ​ለ​ሳል፤ በም​ድ​ሩም በሰ​ይፍ እን​ዲ​ወ​ድቅ አደ​ር​ጋ​ለሁ በሉት” አላ​ቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እነሆ፥ በላዩ መንፈስን እሰድዳለሁ፥ ወሬንም ይሰማል፥ ወደ ምድሩም ይመለሳል፥ በምድሩም በሰይፍ እንዲወድቅ አደርጋለሁ በሉት አላቸው።

Ver Capítulo



ኢሳይያስ 37:7
15 Referencias Cruzadas  

ይህም የሆነበት ምክንያት እግዚአብሔር ሶርያውያንን በፈረሶችና በሠረገሎች የታጀበ የብዙ ሠራዊት ግሥጋሤ የሚመስል ድምፅ አሰምቶአቸው ስለ ነበር ነው፤ ይኸውም ሶርያውያን እንዳሰቡት የእስራኤል ንጉሥ የሒታውያንና የግብጽ ነገሥታትን ከነሠራዊቶቻቸው ቀጥሮ አደጋ ሊጥልባቸው የመጣ መስሎአቸው ነበር።


ጌታም ጽኑዓን ኃያላኑንና መሳፍንቱን የጦር አዛዦቹንም ከአሦር ንጉሥ ሰፈር እንዲያጠፋ መልአኩን ላከ። የአሦርም ንጉሥ አፍሮ ወደ አገሩ ተመለሰ። ወደ አምላኩም ቤት በገባ ጊዜ ከአብራኩ የወጡት ልጆቹ በዚያ በሰይፍ ገደሉት።


የሚያስደነግጥ ድምፅ በጆሮው ነው፥ በሰላምም ሳለ ቀማኛ ይመጣበታል።


በእግዚአብሔር እስትንፋስ ይጠፋሉ፥ በቁጣውም መንፈስ ያልቃሉ።


እንደሚሟሟ ቀንድ አውጣ፥ ፀሐይን እንዳላየ ጭንጋፍ ይሁኑ።


ቁጣህና ትዕቢትህ ወደ ጆሮዬ ደርሶአል፤ ስለዚህ ስናጋዬን በአፍንጫህ ልጓሜንም በከንፈርህ አደርጋለሁ፤ በመጣህበትም መንገድ እመልስሃለሁ።


የአሦርም ንጉሥ፦ “የኢትዮጵያ ንጉሥ ቲርሐቅ ሊዋጋህ መጥቷል” የሚል ወሬ ሰማ። ይህን በሰማም ጊዜ ወደ ሕዝቅያስ መልእክተኞችን ላከ፥ እንዲህም አለው፦