ኢሳይያስ 37:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተም እንዲህ አለክ፦ በሠረገላዬ ብዛት ወደ ተራሮች ከፍታ፥ ወደ ሲባኖስ ጥግ ወጥቻለሁ፤ ረጃጅሞቹን ዝግባዎች፥ የተመረጡትን ጥንዶች እቈርጣለሁ፥ ወደ ከፍታውም ዳርቻ ወደ ቀርሜሎስ ዱር እገባለሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመልእክተኞችህ በኩል፣ በጌታ ላይ ብዙ የስድብ ቃል ተናገርህ፤ እንዲህም አልህ፤ ‘በሠረገሎቼ ብዛት፣ የተራሮችንም ከፍታ፣ የሊባኖስንም ጫፍ ወጥቻለሁ፤ ረዣዥም ዝግባዎችን፣ የተመረጡ ጥዶችን ቈርጫለሁ፤ እጅግ ወደራቁት ከፍታዎች፣ እጅግ ውብ ወደሆኑትም ደኖች ደርሻለሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አገልጋዮችህን ልከህ በጌታ ላይ የስድብ ቃል በመናገር፦ ‘በሠረገሎቼ ብርታት ከፍተኛ የሆኑ የሊባኖስ ተራራዎችን ይዤአለሁ፤ ረጃጅም የሆኑትን የሊባኖስ ዛፎችና የተዋቡ የዝግባ ዛፎችን ቈርጬአለሁ፤ በከፍተኛ ስፍራዎች ላይ ጥቅጥቅ ወዳሉት ደኖች አልፌአለሁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተም በመልእክተኞችህ በኩል እንዲህ ብለህ እግዚአብሔርን ተገዳደርኸው፦ በሰረገላዬ ብዛት ወደ ተራሮች ከፍታ፥ ወደ ሊባኖስ ራስ ወጥቻለሁ፤ ረዣዥሞቹንም ዝግባዎች፥ የተመረጡትንም ጥዶች እቈርጣለሁ፤ ወደ ከፍታውም ዳርቻ ወደ ዱሩ እገባለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተም፦ በሰረገላዬ ብዛት ወደ ተራሮች ከፍታ፥ ወደ ሲባኖስ ጥግ ላይ ወጥቻለሁ፥ ረጃጅሞቹንም ዝግባዎች የተመረጡትንም ጥንዶች እቈርጣለሁ፥ ወደ ከፍታውም ዳርቻ ወደ ቀርሜሎስ ዱር እገባለሁ። |
ምናልባት በሕያው አምላክ ላይ ይገዳደር ዘንድ አለቃው የአሦር ንጉሥ የላከውን የራፋስቂስን ቃል አምላክህ ጌታ ሰምቶ እንደሆነ፥ አምላክህ ጌታም ስለ ሰማው ቃል ይገሥጸው እንደሆን፥ ስለዚህ አንተም በሕይወት ስለተረፉት ቅሬታ ጸልይ አሉት።”
ጌታ ስለ ይሁዳ ንጉሥ ቤት እንዲህ ይላልና፦ አንተ በእኔ ዘንድ እንደ ገለዓድና እንደ ሊባኖስ ራስ ነህ፥ ነገር ግን በእርግጥ ምድረ በዳ ማንም የማይቀመጥባቸውም ከተሞች አደርግሃለሁ።
ግብጽ እንደ ግብጽ ወንዝ ይነሳል ውኃውም እንደ ወንዞች ይናወጣል፤ እርሱም፦ እነሣለሁ ምድርንም ሁሉ እሸፍናለሁ፤ ከተሞችንና የሚኖሩባቸውን አጠፋለሁ ብሏል።