ኢሳይያስ 32:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጽድቅም ሥራ ሰላም፥ የጽድቅም ፍሬ ለዘለዓለም ጸጥታና መታመን ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጽድቅ ፍሬ ሰላም፣ የጽድቅ ውጤትም ጸጥታና ለዘላለም ያለ ሥጋት ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጽድቅ ሥራ ሰላምን ያስገኛል፤ ውጤቱም ዘለዓለማዊ የሕይወቱ ዋስትና ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጽድቅም ሥራ ሰላም ይሆናል፤ ጽድቅም የዕረፍት ቦታን ይይዛል፤ ለዘለዓለምም ይታመኑበታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጽድቅም ሥራ ሰላም፥ የጽድቅም ፍሬ ለዘላለም ጸጥታና መታመን ይሆናል። |
የእስራኤል ቅዱስ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ በመመለስና በማረፍ ትድናላችሁ፤ ኃይላችሁ በጸጥታና በመታመን ይሆናል፤ እናንተ ግን እምቢ አላችሁ፥
ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆም፥ ሰላምን እንደ ወንዝ፥ የአሕዛብንም ክብር እንደሚጐርፍ ፈሳሽ እመልስላታለሁ፤ ከዚያም ትጠባላችሁ፥ በጫንቃ ላይ ይሸከሙአችኋል በጉልበትም ላይ እያስቀመጡ ያቀማጥሏችኋል።
ለአገልጋዬ ለያዕቆብ በሰጠኋት፥ አባቶቻችሁም በኖሩባት ምድር ይኖራሉ፤ እነርሱ፥ ልጆቻቸውና የልጅ ልጆቻቸው ለዘለዓለም በእርሷ ይኖራሉ፤ አገልጋዬ ዳዊት ለዘለዓለም ልዑላቸው ይሆናል።
ትምክህታችን ይህ ነው፦ በዚህ ዓለም ይልቁንም በእናንተ ዘንድ፥ በእግዚአብሔር ጸጋ እንጂ በሥጋዊ ጥበብ ባልሆነ፥ በእግዚአብሔር ቅድስናና ቅንነት እንደኖርን፥ የሕሊናችን ምስክርነት ነው።