ኢሳይያስ 32:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ ዓለመኛ ሴቶች ሆይ፥ በፍርሃት ራዱ፤ ተማምናችሁ የምትቀመጡ፥ ተንቀጥቀጡ፤ ልብሳችሁን አውልቁ፥ ዕራቁታችሁን ሁኑ፥ ወገባችሁንም በማቅ ታጠቁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ ትዕቢት የወጠራችሁ ሴቶች ተንቀጥቀጡ፤ እናንተ ተደላድላችሁ የምትኖሩ ሴቶች ልጆች፣ በፍርሀት ተርበትበቱ! ልብሳችሁን አውልቁ፤ ወገባችሁን በማቅ ታጠቁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስከ አሁን ከሐሳብና ከጭንቀት ነጻ ሆናችሁ በመቀማጠል ትኖሩ ነበር፤ አሁን ግን በፍርሃት ተንቀጥቀጡ! ልብሳችሁን አውልቃችሁ በወገባችሁ ላይ ማቅ ታጠቁ! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተ ተማምናችሁ የምትቀመጡ ደንግጡ፤ ሴቶች ሆይ፥ እዘኑ፤ ልብሳችሁንም አውልቁ፤ ዕራቁታችሁንም ሁኑ፤ ወገባችሁንም በማቅ ታጠቁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ ዓለመኞች ሴቶች ሆይ፥ ተጠንቀቁ፥ ተማምናችሁም የምትቀመጡ ሆይ፥ ተንቀጥቀጡ፥ ልብሳችሁን አውልቁ፥ ዕራቁታችሁን ሁኑ፥ ወገባችሁንም በማቅ ታጠቁ። |
ጌታ ምድርን ለማናወጥ በሚነሣበት ጊዜ፤ ሰዎች ከአስፈሪነቱ እንዲሁም ከግርማው የተነሣ፤ ወደ ድንጋይ ዋሻ፤ ወደ ዐለት ስንጣቂ ሮጠው ይገባሉ።
እንዲሁ የአሦር ንጉሥ የግብጽንና የኢትዮጵያን ምርኮ፥ ጐበዛዝቱንና ሽማግሌዎቹን፥ ራቁታቸውንና ባዶ እግራቸውን አድርጎ ገላቸውንም ገልጦ፥ ለግብጽ ጉስቁልና ይነዳቸዋል።
በጽዮን ያሉ ኃጢአተኞች ፈሩ፤ አምላክ የሌላቸው በፍርሃት ራዱ፤ “ከምትበላ እሳት ጋር መኖርን የሚችል ከእኛ መሀል ማን አለ? ለዘለዓለምም ከምትነድ እሳት ጋር መኖርን የሚችል ከእኛ መሀል ማን አለ?”
አሁንም አንቺ ተድላን የምትወጅ፥ በምቾትም የምትቀመጪ፥ በልብሽም፦ “እኔ ነኝ ከእኔም በቀር ሌላ የለም፤ መበለትም ሆኜ አልኖርም፥ የወላድ መካንነትንም አላውቅም” የምትዪ ይህን ስሚ፤
ሐሴቦን ሆይ! ጋይ ፈርሳለችና አልቅሺ፤ እናንተም የረባት ሴቶች ልጆች ሆይ! ሚልኮም ካህናቱና አለቆቹም በአንድነት ይማረካሉና ጩኹ፥ ማቅም ታጠቁ፥ አልቅሱም፥ በቅጥሮችም መካከል ተርዋርዋጡ።
የሕዝቤ ሴት ልጅ ሆይ! ማቅ ልበሺ፥ በአመድም ውስጥ ተንከባለዪ፤ አጥፊ በላያችን በድንገት ይመጣብናልና ለአንድያ ልጅ እንደሚደረግ ልቅሶ፥ መራራ ልቅሶ አልቅሺ።
ስጋት ሳይኖርባት የተቀመጠች ደስተኛይቱ ከተማ ይህች ናት፥ በልብዋም፦ “እኔ ነኝ፥ ከእኔም በቀር ሌላ የለም” ያለች፥ እንዴት አራዊት የሚመሰጉባት ባድማ ሆነች! በእርሷ በኩል የሚያልፈው ሁሉ እጁን እያወዛወዘ ያፏጫል።
ጌታ የሚያስነሣብህን ጠላቶችህን ታገለግላለህ፤ በራብና በጥማት፥ በእርዛትና በማጣት እስኪያጠፉህም ድረስ በዐንገትህ ላይ የብረት ቀንበር ይጭኑብሃል።