ከሞት የተረፉትም ሶርያውያን ሸሽተው ወደ አፌቅ ከተማ ገቡ፤ በዚያም ቁጥራቸው ኻያ ሰባት ሺህ በሚሆኑት ወታደሮች ላይ የከተማው ቅጽር ተንዶባቸው አለቁ። ቤንሀዳድም አምልጦ ወደ ከተማይቱ በመግባት ከአንድ ቤት በስተ ኋላ በኩል ባለው ክፍል ውስጥ ተደበቀ።
ኢሳይያስ 30:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ይህ በደል አዘብዝቦ ለመፍረስ እንደ ቀረበ፥ አፈራረሱም ፈጥኖ ድንገት እንደሚመጣ እንደ ረጅም ቅጥር ይሆንባችኋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ይህ ኀጢአት፣ ተሰነጣጥቆ ሊወድቅ እንደ ደረሰ፣ ሳይታሰብ ድንገት እንደሚወድቅ ረዥም ቅጥር ይሆንባችኋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ይህ በደላችሁ ተሰነጣጥቆ በማኰፍኰፍ ሊወድቅ እንደ ተቃረበና አወዳደቁም በፍጥነትና በቅጽበት እንደሚደርስበት እንደ ረጅም የቅጽር ግንብ ያደርጋችኋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ ይህ በደል አዘብዝቦ ለመፍረስ እንደ ቀረበ፥ አፈራረሱም ፈጥኖ ድንገት እንደሚመጣ እንደ ከተማ ቅጥር ይሆንባችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ ይህ በደል አዘብዝቦ ለመፍረስ እንደ ቀረበ፥ አፈራረሱም ፈጥኖ ድንገት እንደሚመጣ እንደ ረጅም ቅጥር ይሆንባችኋል። |
ከሞት የተረፉትም ሶርያውያን ሸሽተው ወደ አፌቅ ከተማ ገቡ፤ በዚያም ቁጥራቸው ኻያ ሰባት ሺህ በሚሆኑት ወታደሮች ላይ የከተማው ቅጽር ተንዶባቸው አለቁ። ቤንሀዳድም አምልጦ ወደ ከተማይቱ በመግባት ከአንድ ቤት በስተ ኋላ በኩል ባለው ክፍል ውስጥ ተደበቀ።
ይህም ነገር የሠራዊት ጌታ ይህንን በጆሮዬ ነገረኝ፤ እስክትሞቱ ድረስ ይህ በደል በእውነት አይሰረይላችሁም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
በምድር በሚኖሩት ላይ በበደላቸው ምክንያት ቁጣውን ሊያመጣባቸው፥ እነሆ፥ ጌታ ከስፍራው ይወጣል፤ ምድርም ያፈሰሰችውን ደም ትገልጣለች፥ የተገደሉትንም ከእንግዲህ ወዲህ አትሸሽግም።
ጌታም የሕዝቡን ስብራት በጠገነ ዕለት፥ መቅሰፍቱ የቈሰለውንም በፈወሰ ዕለት፥ የጨረቃ ብርሃን እንደ ፀሐይ ብርሃን፥ የፀሐይም ብርሃን እንደ ሰባት ቀን ብርሃን ሰባት እጥፍ ይሆናል።
በዚህ ምክንያት ክፉ ነገር ይመጣብሻል፥ በምዋርትሽም እንዴት እንደምታርቂው አታውቂም፤ ጉዳት ይወድቅብሻል ልታስወግጂውም አትችይም፤ የማታውቂያትም ጉስቁልና ድንገት ትመጣብሻለች።
ነገር ግን ሰምቶ የማያደርገው ቤቱን ያለ መሠረት በምድር ላይ የሠራ ሰውን ይመስላል፤ ወንዙም ገፋው፤ ወዲያውም ወደቀ የዚያ ቤት አወዳደቅም ታላቅ ሆነ።”