ኢሳይያስ 3:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሽቶ ፈንታ ግማት፤ በሻሽ ፈንታ ገመድ፤ አምሮ በተሠራ ጠጉር ፈንታ ቡሀነት፤ ባማረ ልብስ ፈንታ ማቅ፤ በውበትም ፈንታ ጠባሳ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሽቱ ፈንታ ግማት፣ በሻሽ ፈንታ ገመድ፣ አምሮ በተሠራ ጠጕር ፈንታ ቡሓነት፣ ባማረ ልብስ ፈንታ ማቅ፣ በውበትም ፈንታ ጠባሳ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ በሽቶ ፈንታ ግማት፥ በጥሩ መታጠቂያ ፈንታ ገመድ፥ በጐፈሬ ፈንታ ቡሃነት፥ በመጐናጸፊያ ፈንታ ማቅ፥ በውበትም ፈንታ ጠባሳ መሆን ይመጣባቸዋል! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም ይሆናል፤ ስለ ሥራሽ ክፋት በሽቱ ፋንታ ትቢያ ይሁንብሽ፤ በወርቅ መታጠቂያሽም ፋንታ ገመድ ታጠቂ፤ በራስ ወርቅ ቀጸላሽም ፋንታ ቡሃነት ይውጣብሽ፤ በሐር መጐናጸፊያሽ ፋንታ ማቅ ልበሽ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም ይሆናል፥ በሽቱ ፋንታ ግማት፥ በመታጠቂያውም ፋንታ ገመድ፥ ጠጕርንም በመንቀስ ፋንታ ቡሀነት፥ በመጎናጸፊያ ፋንታ ማቅ፥ በውበትም ፋንታ ጠባሳ ይሆናል። |
ወደ ባይት ወደ ዲቦንም ወደ ኮረብታ መስገጃዎችም ለልቅሶ ወጥተዋል፤ ሞዓብ በናባውና በሜድባ ላይ ታለቅሳለች፤ ራሳቸው ሁሉ ተነጭቶአል፥ ጢማቸውም ሁሉ ተላጭቷል።
ሐሴቦን ሆይ! ጋይ ፈርሳለችና አልቅሺ፤ እናንተም የረባት ሴቶች ልጆች ሆይ! ሚልኮም ካህናቱና አለቆቹም በአንድነት ይማረካሉና ጩኹ፥ ማቅም ታጠቁ፥ አልቅሱም፥ በቅጥሮችም መካከል ተርዋርዋጡ።
የሕዝቤ ሴት ልጅ ሆይ! ማቅ ልበሺ፥ በአመድም ውስጥ ተንከባለዪ፤ አጥፊ በላያችን በድንገት ይመጣብናልና ለአንድያ ልጅ እንደሚደረግ ልቅሶ፥ መራራ ልቅሶ አልቅሺ።
ዮድ። የጽዮን ሴት ልጅ ሽማግሌዎች ዝም ብለው በመሬት ላይ ተቀምጠዋል፥ ትቢያን በራሳቸው ላይ ነሰነሱ፥ ማቅም ታጠቁ፥ የኢየሩሳሌም ደናግል ራሳቸውን ወደ ምድር አዘነበሉ።
እኔ ደግሞ እንዲህ አደርግባችኋለሁ፤ ፍርሃትን፥ ነፍስን የሚያኮስስና ዓይንን የሚያፈዝዝ ክሳትና ትኩሳት አመጣባችኋለሁ፤ ጠላቶቻችሁም ይበሉታልና ዘራችሁን በከንቱ ትዘራላችሁ።
ዓመት በዓላችሁንም ወደ ልቅሶ፥ ዝማሬአችሁንም ወደ ዋይታ እለውጣለሁ፤ ማቅንም በወገብ ሁሉ፥ ጸጉር መላጨትንም በሁሉ ላይ አመጣለሁ፤ እንደ አንድያ ልጅም ልቅሶ፥ ፍጻሜውንም እንደ መራራ ቀን አደርገዋለሁ።
ሰዎችም በታላቅ ትኩሳት ተቃጠሉ፤ በነዚህም መቅሠፍቶች ላይ ሥልጣን ያለውን የእግዚአብሔርን ስም ተሳደቡ፤ ክብርንም እንዲሰጡት ንስሓ አልገቡም።