ኢሳይያስ 3:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ በፍርድ ወንበር ላይ ተቀምጦአል፤ በሕዝቡም ላይ ለመፍረድ ተነሥቶአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር በፍርድ ወንበር ላይ ተቀምጧል፤ በሕዝቡም ላይ ለመፍረድ ተነሥቷል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በፍርድ ዙፋኑ ላይ ተቀምጦአል፤ በሕዝቡም ላይ ለመፍረድ ተዘጋጅቶአል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን እግዚአብሔር ዛሬ ለፍርድ ይነሣል፤ በሕዝቡም ላይ ሊፈርድ ይነሣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር ለፍርድ ተነሥቶአል በሕዝቡም ላይ ሊፈርድ ቆሞአል። |
ስለ ወገኑ የሚምዋገት አምላክሽ ጌታሽ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ የሚያንገደግድን ጽዋ የቁጣዬንም ዋንጫ ከእጅሽ ወስጃለሁ፤ ደግመሽም ከእንግዲህ ወዲህ አትጠጪውም።