ሁሉንም ነገር አዘጋጅቶና ጠብቆ፥ ከእኔ ጋር ዘላለማዊ ኪዳን ያደረገ፥ መዳኔን ከፍጻሜ የሚያደርሰው፥ መሻቴን ሁሉ የሚሰጠኝ እርሱ አይደለምን? በውኑ ቤቴ በእግዚአብሔር ዘንድ እንዲህ አይደለምን?
ኢሳይያስ 26:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ ጌታ፥ በፍርድህ መንገድ ተስፋ አድርገንሃል፥ ስምህም መታሰቢያህም የነፍሳችን ምኞት ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ በሕግህ ጐዳና በመሄድ፣ አንተን ተስፋ አድርገናል፤ ስምህና ዝናህ፣ የልባችን ምኞት ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላክ ሆይ፥ ሕግህን እየጠበቅን በአንተ ተስፋ እናደርጋለን። የልባችንም ምኞት የአንተ ገናናነት በሕዝቦች ዘንድ እንዲታወቅ ማድረግ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔር መንገድ የቀና ነው፤ በቅዱስ ስሙም ታመን፤ ነፍሳችን የተመኘችውንም አገኘን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቤቱ፥ በፍርድህ መንገድ ተስፋ አድርገንሃል፥ ስምህንም መታሰቢያህም የነፍሳችን ምኞት ነው። |
ሁሉንም ነገር አዘጋጅቶና ጠብቆ፥ ከእኔ ጋር ዘላለማዊ ኪዳን ያደረገ፥ መዳኔን ከፍጻሜ የሚያደርሰው፥ መሻቴን ሁሉ የሚሰጠኝ እርሱ አይደለምን? በውኑ ቤቴ በእግዚአብሔር ዘንድ እንዲህ አይደለምን?
እግዚአብሔርም ደግሞ ሙሴን አለው፦ “ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ትላለህ፦ ‘ጌታ የአባቶቻችሁ አምላክ፥ የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅ አምላክ፥ የያዕቆብም አምላክ ወደ እናንተ ላከኝ፤’ ይህ ለዘለዓለሙ ስሜ ነው፥ እስከ ልጅ ልጅ ድረስም መታሰቢያዬ ይህ ነው።”
አቤቱ ጌታ፥ አንተ አምላኬ ነህ፤ አስቀድሞ የታሰበውን፤ ድንቅ ነገር በታማኝነትና በእውነት አድርገሃልና ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ ስምህንም አመሰግናሁ።
በዚያም ቀን፦ እነሆ፥ አምላካችን ይህ ነው፤ ተስፋ አድርገነዋል፥ ያድነንማል፤ ጌታ ይህ ነው፤ ጠብቀነዋል፤ በማዳኑ ደስ ይለናል፤ ሐሤትም እናደርጋለን፥ ይባላል።
ጌታም የፍርድ አምላክ ነው፤ ስለ ሆነም ጌታ ይራራላችኋልና ይታገሣል፤ ሊምራችሁም ከፍ ከፍ ይላል፤ እርሱን በመተማመን የሚጠባበቁ ሁሉ ብፁዓን ናቸው።
ነገሥታትም አሳዳጊ አባቶችሽ ይሆናሉ፥ እቴጌዎቻቸውም ሞግዝቶችሽ ይሆናሉ፤ ግንባራቸውንም ወደ ምድር ዝቅ አድርገው ይሰግዱልሻል፥ የእግርሽንም ትቢያ ይልሳሉ፤ እኔም ጌታ እንደሆንኩ ታውቂያለሽ፤ እኔንም በመተማመን የሚጠባበቁ አያፍሩም።