ኢሳይያስ 24:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እየዘፈኑም የወይን ጠጅን አይጠጡትም፥ የሚያሰክር መጠጥ የሚጠጡት መራራ ይሆንባቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእንግዲህ እየዘፈኑ የወይን ጠጅ አይጠጡም፤ መጠጡም ለሚጠጡት ይመርራል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የወይን ጠጅ እየጠጡ በመዝፈን መደሰት አይኖርም፤ የሚያሰክር መጠጥም ለጠጪው መራራ ይሆናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወይንን የሚጠጡት አፈሩ፤ የሚያሰክር መጠጥም ለሚጠጡት መራራ ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እየዘፈኑም የወይን ጠጅን አይጠጡትም፥ የሚያሰክር መጠጥ ለሚጠጡት መራራ ይሆናል። |
ክፉውን መልካም፤ መልካሙን ክፉ ለሚሉ ብርሃኑን ጨለማ፤ ጨለማውን ብርሃን ለሚያደርጉ፤ ጣፋጩን መራራ፤ መራራውንም ጣፋጭ ለሚያደርጉ ወዮላቸው!
ዓመት በዓላችሁንም ወደ ልቅሶ፥ ዝማሬአችሁንም ወደ ዋይታ እለውጣለሁ፤ ማቅንም በወገብ ሁሉ፥ ጸጉር መላጨትንም በሁሉ ላይ አመጣለሁ፤ እንደ አንድያ ልጅም ልቅሶ፥ ፍጻሜውንም እንደ መራራ ቀን አደርገዋለሁ።
የሠራዊት ጌታ ይጠብቃቸዋል፤ እነርሱም ይውጧቸዋል፥ በድንጋይ ወንጭፍም ያሸንፋሉ፤ ይጠጧቸዋል፥ በወይን ጠጅ እንደ ሰከረ ሰው ይሞቃቸዋል፤ እንደ መሠዊያም ማዕዘኖች፥ እንደ ጥዋዎቹም የተሞሉ ይሆናሉ።