ኢሳይያስ 23:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጥልቅ ውኆቿ ላይ የሺሖር እህልና የዓባይ ወንዝ መከር ገቢዋ ነበር፤ እርሷም የአሕዛብ የንግድ መናኸሪያ ነበረች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በታላላቅ ውሆች ላይ፣ ለጢሮስ የሺሖር እህል ይመጣላት ነበር፤ የአባይ መከር ገቢዋ ነበር፤ እርሷም የመንግሥታቱ የንግድ መናኸሪያ ሆነች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በግብጽ የሚመረተው እህል በትልቁ ባሕር በኩል መጥቶ ለጢሮስ ትልቅ ገቢ ይሆናል፤ ስለዚህ ጢሮስ የዓለም ገበያ ሆናለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የገቡ ስደተኞች አሕዛብ በመከር ጊዜ እንደሚለወጥ ዘር ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሺሖር ዘርና የአባይ ወንዝ መከር በብዙ ውኆች ላይ ገቢዋ ነበረ፥ እርስዋም የአሕዛብ መነገጃ ነበረች። |
አሁንስ የሺሖርን ውኃ ለመጠጣት ወደ ግብጽ በመሄድሽ የምታገኚው ምን ነገር አለ? የኤፍራጥስንም ውኃ ለመጠጣት ወደ አሦር በመሄድሽ የምታገኚው ምን ነገር አለ?
በግብጽ ፊት ለፊት ካለው ከሺሖር ወንዝ ጀምሮ በሰሜን በኩል እስካለችው የከነዓናውያን ሆና እስከ ተቈጠረችው እስከ አቃሮን ዳርቻ ድረስ፥ የጋዛ፥ የአዛጦን፥ የአስቀሎና፥ የጌት፥ የአቃሮን፥ አምስቱ የፍልስጥኤማውያን ገዢዎች ናቸው፥ የኤዋውያን የሆኑትም እንዲሁ፥