ኢሳይያስ 22:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከማዕረግህ አወርድሃለሁ፤ ከሹመትህም ትሻራለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከማዕረግህ አወርድሃለሁ፤ ከኀላፊነትህም ትባረራለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር አንተን ከደረጃህ ዝቅ ያደርግሃል፤ ከሥራህም ያባርርሃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከአዛዥነት ሥራህና ከሥልጣንህ ትሻራለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከአዛዥነት ሥራ አሳድድሃለሁ፥ ከሹመትህም ትሻራለህ። |
የዱር ዛፎች ሁሉ ረጅሙን ዛፍ ዝቅ ያደረግሁ፥ አጭሩንም ዛፍ ከፍ ያደረግሁ፥ የለመለመውንም ዛፍ ያደረቅሁ፥ የደረቀውንም ዛፍ ያለመለምሁ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ፤ እኔ ጌታ ተናግሬአለሁ፥ እኔም አደርጋለሁ።