በዓባይ ወንዝ የነበሩ ዓሦችም ሞቱ፤ የዓባይም ወንዝ ገማ፥ ግብጻውያንም ከዓባይ ወንዝ ውኃ መጠጣት አልቻሉም፤ ደሙም በግብጽ ምድር ሁሉ ላይ ነበረ።
ኢሳይያስ 19:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዓሣ አጥማጆቹ ያዝናሉ፤ በዐባይ ወንዝ ላይ መንጠቆአቸውን የሚጥሉት ሁሉ ያለቅሳሉ፤ በውኆችም ላይ መረብ የሚዘረጉት በድካም ይዝላሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዓሣ አጥማጆች ያዝናሉ፤ በአባይ ወንዝ ላይ መንጠቋቸውን የሚወረውሩ ሁሉ ያለቅሳሉ፤ በውሃ ላይ መረባቸውን የሚጥሉ ሁሉ፣ ጕልበታቸው ይዝላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መንጠቆአቸውን ወደ አባይ ወንዝ የሚጥሉ ዓሣ አጥማጆች ያዝናሉ፤ ያለቅሳሉም፤ መረቦቻቸውንም በውሃ ላይ የሚዘረጉ ተስፋ ይቈርጣሉ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዓሣ አጥማጆቹ ያዝናሉ፤ በዓባይም ወንዝ መቃጥን የሚጥሉት ሁሉ ያለቅሳሉ፤ በውኆችም ላይ መረብ የሚዘረጉት ያለቅሳሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዓሣ አጥማጆቹ ያዝናሉ፥ በዓባይም ወንዝ መቃጥን የሚጥሉት ሁሉ ያለቅሳሉ፥ በውኆችም ላይ መረብ የሚዘረጉት ይዝላሉ። |
በዓባይ ወንዝ የነበሩ ዓሦችም ሞቱ፤ የዓባይም ወንዝ ገማ፥ ግብጻውያንም ከዓባይ ወንዝ ውኃ መጠጣት አልቻሉም፤ ደሙም በግብጽ ምድር ሁሉ ላይ ነበረ።
ከዔንጌዲ ጀምሮ እስከ ዔንዔግላይም ድረስ አጥማጆች በዚያ ይቆማሉ፤ የመረቦች መዘርጊያ ይሆናል፤ ዓሣዎችም እንደ ታላቁ ባሕር ዓሣ በየወገናቸው እጅግ ይበዛሉ።
በግብጽ ሳለን እንዲያው በነጻ እንበላው የነበረውን ዓሣ፥ ዱባውንም፥ ሐብሐብውንም፥ ባሕሮውንም፥ ቀዩንም ሽንኩርት፥ ነጩንም ሽንኩርት እናስታውሳለን፤