La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢሳይያስ 14:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌጥህና የበገናህ ድምፅ ወደ ሲኦል ወረደ፤ በበታችህም ብል ተነጥፎአል፥ ትልም መደረቢያህ ሆኖአል ብለው ይመልሱልሃል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ክብርህ፣ ከነበገና ድምፁ ወደ ሲኦል ወረደ፤ ብሎች ከበታችህ ተነጥፈዋል፤ ትሎችም መደረቢያህ ይሆናሉ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ቀድሞ ስለ ክብርህ በመሰንቆ ይዘመርልህ የነበረው ቆመ፤ አሁን አንተ በትዕቢትህ ወደ ሙታን ዓለም ወረድክ። ስለዚህ አልጋህ ምስጥ፥ ልብስህም የትል መንጋ ሆኖአል።’ ”

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከክ​ብ​ርህ ወደ ሲኦል ወደ​ቅህ፤ በበ​ታ​ች​ህም ብል ተነ​ጥ​ፎ​አል፤ ትልም መደ​ረ​ቢ​ያህ ሆኖ​አል” ብለው ይመ​ል​ሱ​ል​ሃል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ጌጥህና የበገናህ ድምፅ ወደ ሲኦል ወረደ፥ በበታችህም ብል ተነጥፎአል፥ ትልም መደረቢያህ ሆኖአል ብለው ይመልሱልሃል።

Ver Capítulo



ኢሳይያስ 14:11
16 Referencias Cruzadas  

በአፈር ውስጥ በአንድ ላይ ይተኛሉ፥ ትልም ይከድናቸዋል።


አንቺ ጩኸትና ፍጅት የሞላብሽ ከተማ፥ የፈንጠዚያ ከተማ ሆይ፥ በአንቺ ውስጥ የተገደሉት በሰይፍ የተገደሉ አይደሉምን፥ በሰልፍስ የሞቱ አይደሉም?


ስለዚህ ሲኦል ሆዷን አሰፋች፤ አፏንም ያለ ልክ ከፈተች፤ መኳንንቱና ሕዝቡ ከረብሸኞቻቸውና ከጨፋሪዎቻቸው ጋር ወደዚያ ይወርዳሉ።


እንደ ልብስም ብል ይበላቸዋል፥ እንደ በግ ጠጉርም ትል ይበላቸዋል፤ ጽድቄ ግን ለዘለዓለም ማዳኔም ለትውልድ ሁሉ ይሆናል።


ወጥተውም በእኔ ያመፁብኝን ሰዎች ሬሳቸውን ያያሉ፤ ትላቸው አይሞትምና፥ እሳታቸውም አይጠፋምና፤ ለሥጋ ለባሽም ሁሉ አስጸያፊ ነገር ይሆናሉ።


የዘፈንሽን ብዛት አስቆማለሁ፤ የበገናሽ ድምፅ ከእንግዲህ ወዲያ አይሰማም።