ሆሴዕ 8:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም፦ “አምላክ ሆይ! እኛ እስራኤል እናውቅሃለን!” ብለው ወደ እኔ ጮሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤልም፣ ‘አምላካችን ሆይ፤ እኛ እናውቅሃለን!’ እያሉ፣ ወደ እኔ ይጮኻሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም፥ “አምላክ ሆይ! እኛ ሕዝብህ እናውቅሃለን” እያሉ ወደ እኔ ይጮኻሉ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላክ ሆይ! እኛ እስራኤል ዐወቅንህ ብለው ወደ እኔ ይጮኻሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም፦ አምላክ ሆይ፥ እኛ እስራኤል አወቅንህ ብለው ወደ እኔ ይጮኻሉ። |
ነገር ግን ኢዩ እስራኤልን ወደ ኃጢአት የመራውን የንጉሥ ኢዮርብዓምን የኃጢአት መንገድ ከመከተል አልተገታም፤ ኢዩ ራሱ ቀደም ሲል የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም በቤትኤልና በዳን ላቆማቸው የወርቅ ጥጃ ምስሎች መስገዱ አልቀረም።
አለቆችዋ በጉቦ ይፈርዳሉ፥ ካህናቷ በክፍያ ያስተምራሉ፥ ነቢዮችዋ በብር ያሟርታሉ፤ “ጌታ በመካከላችን አይደለምን? ክፉ ነገር በእኛ ላይ አይመጣብንም” እያሉ በጌታ ይደገፋሉ።
ባለቤቱ ተነሥቶ በሩን ከቈለፈ በኋላ፥ እናንተ በውጭ ቆማችሁ ‘ጌታ ሆይ! ጌታ ሆይ! ክፈትልን’ እያላችሁ በሩን ማንኳኳት ትጀምራላችሁ፤ እርሱም መልሶ ‘ከየት እንደ ሆናችሁ አላውቅም’ ይላችኋል።