ሆሴዕ 13:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከተሰማሩ በኋላ ጠገቡ፥ በጠገቡም ጊዜ ልባቸው ታበየ፤ ስለዚህ ረሱኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካበላኋቸው በኋላ ጠገቡ፤ በጠገቡ ጊዜ ታበዩ፤ ከዚያም ረሱኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ወደ መልካሚቱ ምድር በገባችሁ ጊዜ እስክትጠግቡ በልታችሁ እጅግ ታበያችሁ፤ እኔንም ረሳችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከተሰማራችሁ በኋላ ጠገባችሁ፤ በጠገባችሁም ጊዜ ልባችሁ ታበየ፤ ስለዚህም ረሳችሁኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከተሰማሩ በኋላ ጠገቡ፥ በጠገቡም ጊዜ ልባቸው ታበየ፥ ስለዚህ ረሱኝ። |
“በእነዚህ ነገሮች ይቅር የምልሽ እንዴት አድርጌ ነው? ልጆችሽ ትተውኛል፥ አማልክትም ባልሆኑ ምለዋል፤ ካጠገብኋቸውም በኋላ አመነዘሩ በጋለሞቶቹም ቤት ተሰበሰቡ።
እስራኤል ፍሬውን የሚሰጥ የተትረፈረፈ ወይን ነው፤ እንደ ፍሬው ብዛት መሠዊያዎችን አብዝቶአል፤ እንደ ምድሩም ብልጥግና መጠን ሐውልቶችን እያሳመሩ ሠርተዋል።
እናታቸው አመንዝራለች፤ የፀነሰቻቸውም እርሷ አሳፋሪ ነገር አድርጋለች፤ ምክንያቱም፦ እንጀራዬንና ውኃዬን፥ ጥጤንና የተልባ እግሬን፥ ዘይቴንና መጠጤን ከሚሰጡኝ ከውሽሞቼ በኋላ እሄዳለሁ፥ ብላለችና።
ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል፤ አንተም እውቀትን ትተሃልና ለእኔ ካህን እንዳትሆን ትቼሃለሁ፤ የአምላክህንም ሕግ ረስተሃልና እኔ ደግሞ ልጆችህን እረሳለሁ።
እኔም ለኤፍሬም እንደ አንበሳ፥ ለይሁዳም ቤት እንደ አንበሳ ደቦል እሆናለሁና፤ እኔ ራሴ ነጥቄ እሄዳለሁ እወስዳለሁም፥ ሊያድንም የሚችል ማንም የለም።
በመኝታቸው ላይ ሆነው ያለቅሱ ነበር እንጂ በልባቸው ወደ እኔ አልጮኹም፤ ስለ እህልና ስለ ወይን ጠጅ ይሰበሰቡ ነበር፤ በእኔም ላይ ዓመፁ።
እስራኤል ፈጣሪውን ረስቶአል፥ ቤተ መንግሥቶችን ሠርቶአል፤ ይሁዳም የተመሸጉትን ከተሞች አብዝቶአል፤ እኔ ግን በእርሱ ከተሞች ላይ እሳት እልካለሁ፥ የንጉሥ ቅጥሮቹንም ትበላለች።
ለራሳቸው ነገሥታትን አነገሡ፥ ከእኔም ዘንድ አይደለም፤ አለቆችንም ሾሙ፥ እኔም አላወቅሁም፤ ለመጥፊያቸው ከብራቸውና ከወርቃቸው ጣዖታትን ለራሳቸው ሠሩ።