በእስራኤል ነገሥታት መንገድ ግን ሄደሃልና፥ የአክዓብም ቤት እንዳደረገ ይሁዳንና በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን እንዲያመነዝሩ አድርገሃልና፥ ከአንተም የሚሻሉትን የአባትህን ቤት ወንድሞችህን ገድለሃልና፥
ሆሴዕ 1:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ መጀመሪያ በሆሴዕ በተናገረ ጊዜ፥ ጌታ ሆሴዕን፦ “ምድሪቱ ከጌታ ርቃ ታላቅ ዝሙት አድርጋለችና ሂድ፤ አመንዝራን ሴት ውሰድና አግባ፤ የዝሙትም ልጆች ይኑሩህ፥” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር በሆሴዕ መናገር በጀመረ ጊዜ፣ እግዚአብሔር “ምድሪቱ ከእግዚአብሔር ተለይታ ታላቅ ምንዝርና እያደረገች ስለ ሆነ፣ ሄደህ አመንዝራ ሴት አግባ፤ የምንዝርና ልጆችንም ለራስህ ውሰድ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በሆሴዕ አማካይነት ለእስራኤል ሕዝብ ቃሉን ማስተላለፍ ሲጀምር ሆሴዕን እንዲህ አለው፦ “ሕዝቤ ከእኔ ተለይቶ አጸያፊ የሆነ የዝሙት ሥራ በመሥራት ላይ ይገኛል፤ እንግዲህ አንተም ሂድና ዘማዊት ሴት አግባ፤ ከእርስዋም የዝሙት ልጆችን ውለድ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ሆሴዕ የመጣ የእግዚአብሔር የቃሉ መጀመሪያ ይህ ነው፤ እግዚአብሔር ሆሴዕን፥ “ምድሪቱ ከእግዚአብሔር ርቃ ታመነዝራለችና ሂድ፤ ዘማዊቱን ሴትና የዘማዊቱን ልጆች ለአንተ ውሰድ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር መጀመሪያ በሆሴዕ በተናገረ ጊዜ፥ እግዚአብሔር ሆሴዕን፦ ምድሪቱ ከእግዚአብሔር ርቃ ታላቅ ግልሙትና ታደርጋለችና ሂድ፥ ጋለሞታን ሴትና የግልሙትናን ልጆች ለአንተ ውሰድ አለው። |
በእስራኤል ነገሥታት መንገድ ግን ሄደሃልና፥ የአክዓብም ቤት እንዳደረገ ይሁዳንና በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን እንዲያመነዝሩ አድርገሃልና፥ ከአንተም የሚሻሉትን የአባትህን ቤት ወንድሞችህን ገድለሃልና፥
ሕዝቤ ሁለት ክፉ ነገሮችን ሠርቷል፤ እኔን የሕይወት ውኃ ምንጭን ትተውኛል፥ ውኃ መቋጠር የማይችሉ የተሸነቈሩ ጉድጓዶች ለራሳቸው ቆፍረዋል።
“ከጥንት ጀምሮ ቀንበርሽን ሰብረሻል እስራትሽንም በጥሰሻል፤ አንቺም፦ ‘አላገለግልም’ አልሽ፥ ነገር ግን ከፍ ባለው ኮረብታ ሁሉ ላይ ከለምለምም ዛፍ ሁሉ በታች ለማመንዘር ተጋደምሽ።
አንቺስ፦ ‘ራሴን አላረከስኩም በዓሊምንም አልተከተልኩም’ እንዴት ትያለሽ? በሸለቆ ያለውን መንገድሽን ተመልከቺ፥ ምን እንዳደረግሽም እወቂ፤ በመንገዶችዋ ላይ ወድያና ወዲህ የምትቅበዘበዥ ወጣት ግመል ሆነሻል፤
ያመለጡት ተማርከው በሄዱባቸው በአሕዛብ መካከል ሆነው ያስታውሱኛል፤ ምክንያቱም ከእኔ በራቀው አመንዝራ ልባቸውና፥ ጣዖቶቻቸውን በተከተሉ በአመንዝራ ዐይኖቻቸው ተሰብሬአለሁና፥ በክፉ ስራቸውና በርኩሰታቸውም ሁሉ ራሳቸውን ይጸየፋሉ።
እናታቸው አመንዝራለች፤ የፀነሰቻቸውም እርሷ አሳፋሪ ነገር አድርጋለች፤ ምክንያቱም፦ እንጀራዬንና ውኃዬን፥ ጥጤንና የተልባ እግሬን፥ ዘይቴንና መጠጤን ከሚሰጡኝ ከውሽሞቼ በኋላ እሄዳለሁ፥ ብላለችና።
ጌታም እንዲህ አለኝ፦ “የእስራኤል ልጆች ወደ ሌሎች አማልክት ቢመለሱና የዘቢብ ጥፍጥፍን ቢወድዱ እንኳ ጌታ እንደሚወድዳቸው እንዲሁ አንተም ዳግመኛ ሂድ፥ በውሽማዋ የምትወደደውን አመንዝራይትን ሴት ውደድ።”
ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እነሆ፥ ከአባቶችህ ጋር ልታርፍ ነው፤ ይህም ሕዝብ በሚገባበት ምድር በሚገኙ ባዕዳን አማልክት ወዲያውኑ ያመነዝራል። እኔን ይተወኛል፤ ከእነርሱም ጋር የገባሁትን ኪዳን ያፈርሳሉ።