ዕብራውያን 6:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይሄውም እግዚአብሔር ሊዋሽ በማይቻል በሁለት በማይለወጥ ነገር፥ በፊታችን ያለውን ተስፋ ለመያዝ ለሸሸን ለእኛ ብርቱ መጽናናት እንዲሆንልን ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ከቶ ሊዋሽ አይችልም፤ እርሱ በሁለት በማይለወጡ ነገሮች በፊታችን ያለውን ተስፋ ለመያዝ ወደ እርሱ ለሸሸን ለእኛ ብርቱ መጽናናት እንድናገኝ አድርጓል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚሁ ዐይነት እግዚአብሔር የማይለወጡትንና የማይዋሽባቸውን ሁለቱን ነገሮች፥ ማለትም ተስፋውንና መሐላውን ሰጥቶናል፤ በእነዚህም በሁለቱ ነገሮች አማካይነት በፊታችን ያለውን ተስፋ አጥብቀን መያዝ እንድንችል መጠጊያ ለማግኘት ወደ እርሱ የሸሸን እኛ ታላቅ መጽናናትን እናገኛለን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔር ቃል ሐሰት ሊሆን አይቻልም፤ በእርሱ ለተማፀን ተጠብቆልን ባለ ተስፋችንም ማመንን ላጸናን ለእኛ ታላቅ ደስታ አለን። |
በአንድ በኩል የአዶንያስ ደጋፊ፥ በሌላ በኩል ደግሞ የአቤሴሎም ተቃዋሚ የሆነው ኢዮአብ የተፈጸመውን ነገር ሁሉ ሰማ፤ ስለዚህም ሸሽቶ ወደ ጌታ ድንኳን ሄደ፤ በዚያም የመሠዊያውን ቀንዶች ይዞ ተማጠነ።
ሐሰትን ይናገር ዘንድ እግዚአብሔር ሰው አይደለም፥ ይጸጸትም ዘንድ የሰው ልጅ አይደለም። እርሱ ያለውን አያደርገውምን? የተናገረውንስ አይፈጽመውምን?
ብዙ ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን ወደ እርሱ ጥምቀት ሲመጡ ባየ ጊዜ፥ እንዲህ አላቸው “እናንተ የእፉኝት ልጆች፥ ከሚመጣው ቁጣ እንድታመልጡ ማን አመለከታችሁ?
እነሆም፥ በኢየሩሳሌም ስምዖን የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤ ይህም ሰው የእስራኤልን መጽናናት የሚጠብቅ፥ ጻድቅና ትጉህም ነበረ፤ መንፈስ ቅዱስም በእርሱ ላይ ነበረ።
እርሱንም እግዚአብሔር በእምነት የሚገኝ በደሙም የሆነ ማስተስሪያ አድርጎ ያቀረበው ነው፤ ይህም በእግዚአብሔር ትዕግስት በፊት የተደረገውን ኃጢአት በመተው ጽድቁን እንዲያሳይ ነው፤
በጭራሽ! “በቃልህ እውነተኛ እንድትሆን፥ ለፍርድ በቀረብክም ጊዜ አሸናፊ እንድትሆን፤” ተብሎ እንደ ተጻፈ፤ ሰው ሁሉ ሐሰተኛ ቢሆንም፥ እግዚአብሔር ግን እውነተኛ ይሁን።
ይህም የሚሆነው ተመሥርታችሁና ተደላድላችሁ ከሰማችሁትም ከወንጌል ተስፋ ሳትናወጡ በእምነት የምትጸኑ ከሆነ ነው፤ ይህም ወንጌል ከሰማይ በታች ባለው ፍጥረት ሁሉ ዘንድ የተሰበከ ነው፤ እኔም ጳውሎስ የእርሱ አገልጋይ ሆንሁ።
ለእነርሱም እግዚአብሔር በአሕዛብ ዘንድ ያለው የዚህ ምሥጢር ክብር ባለጠግነት ምን እንደሆነ ሊያሳውቅ ወደደ፤ ምሥጢሩም የክብር ተስፋ የሆነው በእናንተ ያለው ክርስቶስ ነው።
ይህም እምነትና ፍቅር በሰማይ በተዘጋጀላችሁ ተስፋ ላይ የተመሠረተ ነውና፤ ስለዚህም ተስፋ የእውነት ቃል በሆነው በወንጌል አስቀድማችሁ ሰማችሁ።
ኖኅ ገና ስለማይታየው ነገር ተረድቶ እግዚአብሔርን እየፈራ ቤተ ስዎቹን ለማዳን መርከብን በእምነት አዘጋጀ፤ በዚህም ዓለምን ኰነነ፤ በእምነትም የሚገኘውን ጽድቅ ወራሽ ሆነ።
እነዚያ ከዚህ በፊት ካህናት የሆኑት ያለ መሐላ ነው፤ እርሱ ግን ከመሐላ ጋር ካህን ሆኖአልና፤ “ጌታ ሐሳቡን አይቀይርም ‘አንተ እንደ መልከጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ካህን ነህ፤’ ብሎ ምሏል፥፥”
በእግዚአብሔር ልጅ የሚያምን በራሱ ምስክር አለው፤ እግዚአብሔርን የማያምን ግን እግዚአብሔር ስለ ልጁ የመሰከረውን ምስክርነት ስላላመነ ሐሰተኛ አድርጎታል።