La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዕብራውያን 2:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሁሉን ከእግሮቹ በታች አስገዛህለት፤” ሁሉን ከእርሱ በታች ባስገዛ ጊዜ ያልተገዛለት ምንም አልተወምና። አሁን ግን ሁሉ እንደ ተገዛለት ገና አላየንም፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሁሉን ከእግሮቹ በታች አስገዛህለት።” እግዚአብሔር ሁሉን ከበታቹ ሲያስገዛለት፣ ያላስገዛለት ምንም ነገር የለም፤ ይሁን እንጂ በአሁኑ ጊዜ ሁሉም ተገዝቶለት አናይም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሁሉን ነገር በሥልጣኑ ሥር አደረግህለት።” ሁሉን ነገር በሥልጣኑ ሥር ሲያደርግ፤ በሥልጣኑ ሥር ሳያደርግለት ያስቀረው ምንም ነገር የለም። ነገር ግን አሁን እንዳለ ሁሉ ነገር በእርሱ ሥልጣን ሥር እንደ ሆነ ገና አላየንም።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሁሉ​ንም ከእ​ግሩ በታች አድ​ር​ገህ አስ​ገ​ዛ​ህ​ለት።” ሁሉን ለእ​ርሱ ባስ​ገ​ዛ​ለት ጊዜም የተ​ወ​ውና ያላ​ስ​ገ​ዛ​ለት የለም፤ አሁን ግን ሁሉን እን​ዳ​ስ​ገ​ዛ​ለት አና​ይም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሁሉን ከእግሮቹ በታች አስገዛህለት ብሎ መሰከረ። ሁሉን ከእርሱ በታች ባስገዛ ጊዜ ያልተገዛለት ምንም አልተወምና። አሁን ግን ሁሉ እንደ ተገዛለት ገና አናይም፤

Ver Capítulo



ዕብራውያን 2:8
19 Referencias Cruzadas  

እኔ ግን ንጉሤን ሾምሁ በተቀደሰው ተራራዬ በጽዮን ላይ።


ከመላእክት እጅግ ጥቂት አሳነስኸው፥ በክብርና በምስጋና ዘውድ ከለልኸው።


ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ አላቸው “ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጥቶኛል።


ኢየሱስ አብ ሁሉን በልጁ እንደሰጠው፥ ከእግዚአብሔርም እንደ ወጣና ወደ እግዚአብሔርም እንደሚሄድ አውቆ፥


አባት ልጁን ይወዳል፥ ሁሉንም በእጁ ሰጥቶታል።


“ሁሉን ነገር ከእግሩ ሥር አስገዝቶለታል” ተብሏልና፤ ነገር ግን፥ ሁሉን ነገር አስገዛለት ሲል፥ ሁሉ ነገር በክርስቶስ ሥር እንዲገዛ ያደረገውን እግዚአብሔርን እንደማይጨምር ግልጽ ነው።


ነገር ግን ከመላእክት፥ “ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ፤” ከቶ ለማን ብሎአል?


በእነዚህ በኋለኞቹ ዘመናት ግን፥ ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ ለእኛ ተናገረን፥፥


ስለ እርሱ የምንናገርለት፥ የሚመጣውን ዓለም ያስገዛው ለመላእክት አይደለምና።


እርሱም ወደ ሰማይ ሄዶ በእግዚአብሔር ቀኝ አለ፤ መላእክትና ሥልጣናት ኀይላትም ተገዝተውለታል።


ሕያውም እኔ ነኝ፤ ሞቼም ነበርሁ፤ እነሆም ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ድረስ ሕያው ነኝ፤ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ።


እንዲሁም ከታመነው ምስክር፥ ከሙታን በኩር ከሆነው፥ የምድርም ነገሥታት ገዥ ከሆነው ከኢየሱስ ክርስቶስ፤ ለወደደን፥ ከኀጢአታችንም በደሙ ላጠበን፥