ዮሴፍም ወንድሞቹን፦ “እኔ እሞታለሁ፥ እግዚአብሔርም መጎብኘትን ይጎበኛችኋል፥ ከዚህችም ምድር ያወጣችኋል፥ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም ወደ ማለላቸው ምድር ያደርሳችኋል” አላቸው።
ዕብራውያን 2:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲያውም በአንድ ስፍራ እንዲህ ተብሎ ተመስክሯል፦ “ታስበው ዘንድ ሰው ምንድነው? ወይስ ትጠነቀቅለት ዘንድ የሰው ልጅ ምንድነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን አንዱ በሌላ ስፍራ እንዲህ ብሎ መስክሯል፤ “በሐሳብህ ስፍራ ትሰጠው ዘንድ ሰው ምንድን ነው? ትጠነቀቅለትም ዘንድ የሰው ልጅ ምንድን ነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲያውም በቅዱሳት መጻሕፍት በአንድ ስፍራ እንዲህ ተብሎአል፦ “አንተ እርሱን ታስበው ዘንድ ሰው ምንድን ነው? ለእርሱስ ትጠነቀቅለት ዘንድ የሰው ልጅ ምንድን ነው? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን መጽሐፍ እንዲህ ብሎ የመሰከረበት ስፍራ አለ፤ “ታስበው ዘንድ ሰው ምንድን ነው? ትጐበኘውስ ዘንድ የሰው ልጅ ምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን አንዱ በአንድ ስፍራ፦ ታስበው ዘንድ ሰው ምንድር ነው? ወይስ ትጎበኘው ዘንድ የሰው ልጅ ምንድር ነው? |
ዮሴፍም ወንድሞቹን፦ “እኔ እሞታለሁ፥ እግዚአብሔርም መጎብኘትን ይጎበኛችኋል፥ ከዚህችም ምድር ያወጣችኋል፥ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም ወደ ማለላቸው ምድር ያደርሳችኋል” አላቸው።
ሁሉንም ፍርሃት ያዛቸው፤ እግዚአብሔርንም እንዲህ እያሉ አመሰገኑ፦ “ታላቅ ነቢይ በእኛ መካከል ተነሥቶአል!” “እግዚአብሔርም ሕዝቡን ጐብኝቶአል!”
አስቀድመን ደግሞ እንደ ነገርናችሁና እንደ መሰከርንላችሁ፥ ጌታ ስለዚህ ነገር ሁሉ የሚበቀል ነውና፥ ማንም በዚህ ነገር አይተላለፍ፤ ወንድሙንም አያታልል።
በእነርሱ ውስጥ የነበረው የክርስቶስ መንፈስ፥ ስለ ክርስቶስ መከራ እና ከእርሱም በኋላ ስለሚመጣው ክብር አስቀድሞ ሲመሰክር፥ ምን ወይም እንዴት ባለ ዘመን እንዳመለከተ ይመረምሩ ነበር።