ዕንባቆም 3:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፀዳሉም እንደ ብርሃን ነው፥ ጨረር ከእጁ ወጥቶአል፤ ኃይሉም በዚያ ተሰውሮአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጸዳሉ እንደ ፀሓይ ብርሃን ነው፤ ጨረር ከእጁ ወጣ፤ ኀይሉም በዚያ ተሰውሯል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብርሃኑ እንደ ፀሐይ ብርሃን ነው ኀይሉን ከሸፈነው እጁም የብርሃን ጮራ ይወጣል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፀዳሉም እንደ ብርሃን ነው፣ ጨረር ከእጁ ወጥቶአል፣ ኃይሉም በዚያ ተሰውሮአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፀዳሉም እንደ ብርሃን ነው፥ ጨረር ከእጁ ወጥቶአል፥ ኃይሉም በዚያ ተሰውሮአል። |
ወገቡ ከሚመስለው ወደ ላይ የሚያንጸባርቅ ነገር የሚመስል፥ ቤቱም በእሳት የተከበበ የሚመስል አየሁ፥ ወገቡ ከሚመስለው ወደ ታች ደግሞ በዙሪያው ብርሃን ያለው እሳት የሚመስል አየሁ።
እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ እርሱን ከቶ ማንም አላየውም፤ ማንም ሊያየውም አይችልም፤ ለእርሱ ክብርና የዘለዓለም ኃይል ይሁን፤ አሜን።
ከእንግዲህም ወዲህ ሌሊት አይሆንም፤ ጌታ አምላክም በእነርሱ ላይ ያበራላቸዋልና የመብራት ብርሃንና የፀሐይ ብርሃን አያስፈልጋቸውም፤ ከዘለዓለምም እስከ ዘለዓለም ይነግሣሉ።