የመሥዋዕቱም መዓዛ ጌታን ደስ አሰኘው፤ ጌታም በሐሳቡ እንዲህ አለ፥ “ገና ከታናሽነቱ ጊዜ ጀምሮ የሰው ሐሳብ ክፉ ነውና፥ ሰው በሚፈጽመው በደል ምክንያት ከእንግዲህ ወዲህ ምድርን አልረግምም፤ አሁን እንዳደረግሁት ሕይወት ያለውን ፍጥረት ሁሉ ከእንግዲህ ወዲህ ከቶ አላጠፋም።
ዘፍጥረት 9:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእኔና በእናንተ፥ ሕያው ነፍስ ባለውም ፍጥረት መካከል ያለውን ቃል ኪዳኔን አስባለሁ፤ ውኃም ዳግመኛ ፍጥረትን ሁሉ ያጠፋ ዘንድ የውኃ ሙላት አይመጣም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእናንተና ከሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ ጋራ የገባሁትን ኪዳን ዐስባለሁ፤ ሕይወት ያለውንም ሁሉ ያጠፋ ዘንድ፣ ከእንግዲህ የጥፋት ውሃ ከቶ አይመጣም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ‘ከእንግዲህ ወዲህ የጥፋት ውሃ፤ ሕያዋን ፍጥረቶችን ሁሉ ከቶ አያጠፋም’ ብዬ ከእናንተና ከሌሎች ሕያዋን ፍጥረቶች ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን አስታውሳለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእኔና በእናንተ መካከል፥ ሕያው ነፍስ ባለውም ሥጋ ሁሉ መካከል ያለውን ቃል ኪዳኔን አስባለሁ፤ ሥጋ ያለውንም ሁሉ ያጠፋ ዘንድ ዳግመኛ የጥፋት ውኃን አላመጣም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእኔና በእናንተ መካከል፥ ሕያው ነፍስ ባለውም ሥጋ ሁሉ መካከል ያለውን ቃል ኪዳኔን አስባለሁ፤ ሥጋ ያለውንም ሁሉ ያጠፉ ዘንድ ዳግመኛ የጥፋት ውኃ አይሆንም። |
የመሥዋዕቱም መዓዛ ጌታን ደስ አሰኘው፤ ጌታም በሐሳቡ እንዲህ አለ፥ “ገና ከታናሽነቱ ጊዜ ጀምሮ የሰው ሐሳብ ክፉ ነውና፥ ሰው በሚፈጽመው በደል ምክንያት ከእንግዲህ ወዲህ ምድርን አልረግምም፤ አሁን እንዳደረግሁት ሕይወት ያለውን ፍጥረት ሁሉ ከእንግዲህ ወዲህ ከቶ አላጠፋም።
ይህም ከእናንተ ጋር ላሉትም ሕያው ነፍስ ላላቸው ሁሉ፥ ከእናንተ ጋር ከመርከብ ለወጡት አእዋፍ፥ ለእንስሳትም፥ ለምድር አራዊትም ሁሉ፥ ለየትኛውም የምድር አራዊት ሁሉ ይሆናል።
ቃል ኪዳኔንም ለእናንተ እመሰርታለሁ፥ ሕያው ፍጥረት ሁሉ ዳግመኛ በጥፋት ውኃ አይጠፉም፥ ምድርንም ለማጥፋት ዳግመኛ የጥፋት ውኃ አይመጣም።”
እንዲህም አለ፦ “የእስራኤል አምላክ ጌታ ሆይ! በላይ በሰማይ በታችም በምድር አንተን የሚመስል አምላክ የለም፥ በፍጹም ልባቸው በፊትህ ለሚሄዱ አገልጋዮችህ ቃል ኪዳንንና ምሕረትን የምትጠብቅ፤
“አሁንም አምላካችን ሆይ፥ ቃል ኪዳንና ምሕረትን የምትጠብቅ ታላቅና ኃያል የተፈራኸውም አምላክ ሆይ፥ ከአሦር ነገሥታት ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በእኛና በነገሥታቶቻችን በአለቆቻችንም በካህናቶቻችንም በነብዮቻችንም በአባቶቻችንም በሕዝብህ ሁሉ ላይ የደረሰው መከራ ሁሉ በፊትህ ጥቂት መስሎ አይታይህ።
የእስራኤል ልጆች የመታሰቢያ ድንጋዮች እንዲሆኑ ሁለቱን ዕንቁዎች በኤፉዱ ትከሻዎች ላይ ታደርጋለህ፤ አሮንም በሁለቱ ትከሻዎቹ ላይ ለመታሰቢያ እንዲሆን ስማቸውን በጌታ ፊት ይሸከማል።
አንተም ጌታ አምላካችሁ እርሱ እግዚአብሔር እንደሆነ፥ ለሚወዱትም ትእዛዙንም ለሚጠብቁ ቃል ኪዳኑንና ምሕረቱን እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ የሚጠብቅ የታመነ አምላክ እንደሆነ እወቅ፤