Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሕዝቅኤል 16:60 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

60 ነገር ግን በልጅነትሽ ወራት ከአንቺ ጋር የመሠረትኩትን ቃል ኪዳኔን አስባለሁ፥ የዘለዓለምንም ቃል ኪዳን አቆማለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

60 ነገር ግን በልጅነትሽ ጊዜ ከአንቺ ጋራ የገባሁትን ቃል ኪዳን ዐስባለሁ፤ ለዘላለምም የሚኖር ቃል ኪዳን ከአንቺ ጋራ እመሠርታለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

60 ነገር ግን በወጣትነትሽ ወራት ከአንቺ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን አስታውሳለሁ። ከአንቺ ጋርም የዘለዓለሙን ቃል ኪዳን አጸናለሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

60 ነገር ግን በሕ​ፃ​ን​ነ​ትሽ ወራት ከአ​ንቺ ጋር ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ቃል ኪዳ​ኔን ዐስ​ባ​ለሁ፤ የዘ​ለ​ዓ​ለ​ም​ንም ቃል ኪዳን አጸ​ና​ል​ሻ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

60 ነገር ግን በሕፃንነትሽ ወራት ከአንቺ ጋር ያደረግሁትን ቃል ኪዳኔን አስባለሁ የዘላለምንም ቃል ኪዳን አጸናልሻለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 16:60
24 Referencias Cruzadas  

የአዲስም ኪዳን መካከለኛ ወደሚሆን ወደ ኢየሱስ፥ ከአቤልም ደም ይልቅ የሚሻለውን ወደሚናገር ወደ መርጨት ደም ደርሳችኋል።


ከዚያ ጊዜ በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነው፥ ይላል ጌታ፤ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ፤ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፤ እኔም አምላክ እሆንላቸዋለሁ፤ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑልኛል።


በአንቺ በኩል አለፍሁ፥ አየሁሽም፥ እነሆ ጊዜሽ የፍቅር ጊዜ ነበር፥ እኔም መጐናጸፊያዬን በላይሽ ላይ ዘረጋሁና ዕርቃንሽን ሸፈንሁ፥ ማልሁልሽም ከአንቺም ጋር ቃል ኪዳን ገባሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ አንቺም የእኔ ሆንሽ።


ፊታቸውንም ወደዚያ አቅንተው፦ ኑ፥ ከቶ በማይረሳ በዘለዓለም ቃል ኪዳን ከጌታ ጋር በአንድነት እንሁን፥ ብለው ወደ ጽዮን የሚወስደውን መንገድ ይጠይቃሉ።


ጆሮአችሁን አዘንብሉ ወደ እኔም ቅረቡ፤ ሰውነታችሁ በሕይወት እንድትኖር ስሙኝ፥ የታመነችይቱን የዳዊትን ምሕረት፥ የዘለዓለምን ቃል ኪዳን ከእናንተ ጋር አደርጋለሁ።


ለእነርሱም ኪዳኑን አሰበ፥ እንደ ጽኑ ፍቅሩም ብዛት ተጸጸተ።


እኔም ለያዕቆብ የማልሁትን ቃል ኪዳኔን አስታውሳለሁ፤ እንዲሁም ለይስሐቅና ለአብርሃም የማልሁትንም ቃል ኪዳኔን አስታውሳለሁ፤ ምድሪቱንም አስታውሳለሁ።


በዘላለም ኪዳን ደም የበጎች ታላቅ እረኛ የሆነውን ጌታችን ኢየሱስን ከሞት ያስነሣው የሰላም አምላክ፥


እንዲሁም ለአባቶቻችን ምሕረትን አደረገ፤ ቅዱስ ኪዳኑንም


በበኣሊም የበዓል ቀኖች ዕጣን ለእነርሱ በማጠንዋና ራስዋን በጉትቾችዋና በጌጥዋ በማስጌጥ ውሽሞችዋን ተከትላ እኔን በመርሳትዋ እቀጣታለሁ፥ ይላል ጌታ።


“ሂድ፥ በኢየሩሳሌም ጆሮዎች ላይ አውጅ፥ እንዲህም በል፦ ጌታ እንዲህ ይላል፦ የብላቴንነትሽን ጽኑ ፍቅር የታጨሽበትንም ፍቅር፥ በምድረ በዳ ዘር ባልተዘራበት ምድር እንደ ተከተልሽኝ አስታውሼዋለሁ።


ቃል ኪዳኑን ለዘለዓለም፥ እስከ ሺህ ትውልድ ያዘዘውን ቃሉን አሰበ፥


ሁሉንም ነገር አዘጋጅቶና ጠብቆ፥ ከእኔ ጋር ዘላለማዊ ኪዳን ያደረገ፥ መዳኔን ከፍጻሜ የሚያደርሰው፥ መሻቴን ሁሉ የሚሰጠኝ እርሱ አይደለምን? በውኑ ቤቴ በእግዚአብሔር ዘንድ እንዲህ አይደለምን?


እኔ አምላክ እንድሆናቸው አሕዛብ እያዩ ከግብጽ ምድር ካወጣኋቸው ከአባቶቻቸው ጋር ያለኝን ቃል ኪዳን ስለ እነርሱ አስታውሳለሁ፤ እኔ ጌታ ነኝ።”


በእኔና በእናንተ፥ ሕያው ነፍስ ባለውም ፍጥረት መካከል ያለውን ቃል ኪዳኔን አስባለሁ፤ ውኃም ዳግመኛ ፍጥረትን ሁሉ ያጠፋ ዘንድ የውኃ ሙላት አይመጣም።


ከእነርሱ ጋር የሰላምን ቃል ኪዳን እገባለሁ፥ ክፉ አራዊትን ከምድሪቱ አጠፋለሁ፤ በሰላምም በምድረ በዳ ይኖራሉ በዱርም ውስጥ ይተኛሉ።


ጌታ ግን ያዕቆብን ይምረዋል፥ እስራኤልንም ደግሞ ይመርጠዋል፥ በአገራቸውም ያኖራቸዋል፤ መጻተኛም ከእርሱ ጋር ይተባበራል፥ ከያዕቆብም ቤት ጋር ይተሳሰራል።


እኔ ጌታ ፍትህን የምወድ፥ ስርቆትንና በደልን የምጠላ ነኝ፤ ፍዳቸውንም በእውነት እሰጣቸዋለሁ፥ ከእነርሱም ጋር የዘለዓለምን ቃል ኪዳን አደርጋለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios