La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 49:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ቁጣቸው ርጉም ይሁን፥ ጽኑ ነበርና፥ ኩርፍታቸውም፥ ብርቱ ነበርና፥ በያዕቆብ እከፋፍላቸዋለሁ፥ በእስራኤልም እበታትናቸዋለሁ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እጅግ አስፈሪ የሆነ ቍጣቸው፣ ጭከና የተሞላ ንዴታቸው የተረገመ ይሁን፤ በያዕቆብ እበትናቸዋለሁ፤ በመላው እስራኤልም አሠራጫቸዋለሁ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እጅግ አስፈሪ የሆነ ቊጣቸው፥ እጅግ ጨካኝ የሆነ መዓታቸው፥ የተረገመ ይሁን። በእስራኤል ምድር ሁሉ እበታትናቸዋለሁ፤ በሕዝቡም መካከል እከፋፍላቸዋለሁ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ቍጣ​ቸው ርጉም ይሁን፤ ጽኑ ነበ​ርና፤ ኵር​ፍ​ታ​ቸ​ውም ብርቱ ነበ​ርና፤ በያ​ዕ​ቆብ እከ​ፋ​ፍ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም እበ​ታ​ት​ና​ቸ​ዋ​ለሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ቍጣቸው ርጉም ይሁን ጽኑ ነበርና ኵርፍታቸውም ብርቱ ነበርና፤ በያዕቆብ እከፋፍላቸዋለሁ፥ በእስራኤልም እበታትናቸዋለሁ።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 49:7
11 Referencias Cruzadas  

ከዚያም በኋላ አምኖን ፈጽሞ ጠላት፥ አስቀድሞም ሲወዳት ከነበረው ፍቅሩ ይልቅ በኋላ የጠላት ጥላቻ አየለ። አምኖንም፥ “ተነሽ ውጭልኝ!” አላት።


ከይሁዳም ልጆች ነገድ፥ ከስምዖንም ልጆች ነገድ፥ ከብንያምም ልጆች ነገድ፥ እነዚህን በስማቸው የተጠሩትን ከተሞች በዕጣ ሰጡ።


ድንጋይ ከባድ ነው አሸዋም እንዲሁ፥ ከሁለቱ ግን የሞኝ ቁጣ ይከብዳል።


ቁጡ ሰው ክርክርን ያነሣሣል። ወፈፍተኛ ሰውም ኃጢአትን ያበዛል።


ከእስራኤል ልጆች ርስት ለሌዋውያን የምትሰጡአቸውን ከተሞች እንዲሁ ስጡ፤ ከብዙዎቹ ብዙ፥ ከጥቂቶቹ ጥቂት ትወስዳላችሁ፤ እያንዳንዱ እንደ ወረሱት እንደ ርስታቸው መጠን ከከተሞቻቸው ለሌዋውያን ይሰጣሉ።”