ዘፍጥረት 48:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስራኤልም ዮሴፍን፦ “ፊትህን አያለሁ ብዬ አላሰብሁም ነበር፥ እነሆም እግዚአብሔር ዘርህን ደግሞ አሳየኝ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤልም ዮሴፍን፣ “ዐይንህን እንደ ገና አያለሁ ብዬ አላሰብኩም ነበር፤ እግዚአብሔር ግን ልጆችህን ጭምር ለማየት አበቃኝ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮሴፍንም “አንተን እንደገና አያለሁ ብዬ አላሰብኩም ነበር፤ እግዚአብሔር ግን አንተን ብቻ ሳይሆን ልጆችህንም ጭምር አሳየኝ” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስራኤልም ዮሴፍን፥ “ከፊትህ አልተለየሁም፤ እነሆም፥ እግዚአብሔር ዘርህን ደግሞ አሳየኝ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስራኤልም ዮሴፍን፦ ፊትህን አያለሁ ብዬ አላሰብሁም ነበር እነሆም እግዚአብሔር ዘርህን ደግሞ አሳየኝ አለው። |
ወንዶች ልጆቹና ሴቶች ልጆቹም ሁሉ ሊያጽናኑት ተነሡ፥ መጽናናትን እንቢ አለ፥ እንዲህም አለ፦ “ወደ ልጄ ወደ ሙታን ስፍራ እያዘንሁ እወርዳለሁ።” አባቱም እንደዚህ ስለ እርሱ አለቀሰ።
አባታቸው ያዕቆብም፥ “ያለ ልጅ እኮ አስቀራችሁኝ፤ ዮሴፍ የለም፤ ስምዖንም የለም፤ አሁን ደግሞ ብንያምን ልትወስዱ ትፈልጋላችሁ፤ ኧረ ምን ጉድ ነው የመጣብኝ!” አላቸው።
እንዲህም ብለው ነገሩት፦ “ዮሴፍ ገና በሕይወቱ አለ፥ እርሱም በግብጽ ምድር ላይ ሁሉ ገዥ ሆኖአል።” ያዕቆብም ልቡ ደነገጠ፥ ሊያምናቸውም አልቻለም።