Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 45:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 እንዲህም ብለው ነገሩት፦ “ዮሴፍ ገና በሕይወቱ አለ፥ እርሱም በግብጽ ምድር ላይ ሁሉ ገዥ ሆኖአል።” ያዕቆብም ልቡ ደነገጠ፥ ሊያምናቸውም አልቻለም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 አባታቸውንም፣ “እነሆ ዮሴፍ በሕይወት አለ፤ እንዲያውም በግብጽ ምድር ሁሉ ገዥ ሆኗል” ብለው ነገሩት። ያዕቆብም በድንጋጤ ክው አለ፤ ሊያምናቸውም አልቻለም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 እዚያም እንደ ደረሱ አባታቸውን “ዮሴፍ በሕይወት አለ፤ እንዲያውም በመላው ግብጽ ላይ አስተዳዳሪ ሆኖአል” አሉት። ያዕቆብ ግን እጅግ ደነገጠ፤ ሊያምናቸውም አልቻለም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 እን​ዲ​ህም ብለው ነገ​ሩት፥ “ልጅህ ዮሴፍ በሕ​ይ​ወቱ ነው፤ እር​ሱም በግ​ብፅ ምድር ሁሉ ላይ ገዥ ሆኖ​አል።” ያዕ​ቆ​ብም ልቡ ደነ​ገጠ፤ አላ​መ​ና​ቸ​ው​ምም፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 እንዲህም ብለው ነገሩት፦ ዮሴፍ ገና በሕይወት ነው እርሱም በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ ገዥ ሆኖአል። ያዕቆብም ልቡ ደነገጠ አላመናቸውም ነበርና።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 45:26
17 Referencias Cruzadas  

የዮሴፍንም ቀሚስ ወሰዱ፥ የፍየል አውራም አርደው ቀሚሱን በደም ነከሩት።


ወንዶች ልጆቹና ሴቶች ልጆቹም ሁሉ ሊያጽናኑት ተነሡ፥ መጽናናትን እንቢ አለ፥ እንዲህም አለ፦ “ወደ ልጄ ወደ ሙታን ስፍራ እያዘንሁ እወርዳለሁ።” አባቱም እንደዚህ ስለ እርሱ አለቀሰ።


በከነዓን ምድር ወዳለው ወደ አባታቸው ወደ ያዕቆብ ከደረሱ በኋላ፥ ያጋጠማቸውን ሁሉ እንዲህ ብለው ነገሩት፤


አባታቸው ያዕቆብም፥ “ያለ ልጅ እኮ አስቀራችሁኝ፤ ዮሴፍ የለም፤ ስምዖንም የለም፤ አሁን ደግሞ ብንያምን ልትወስዱ ትፈልጋላችሁ፤ ኧረ ምን ጉድ ነው የመጣብኝ!” አላቸው።


ያዕቆብም፥ “ልጄ አብሮአችሁ ወደዚያ አይወርድም፤ ወንድሙ እንደሆን ሞቷል፤ የቀረው እርሱ ብቻ ነው። ይዛችሁት ስትሄዱ በመንገድ ላይ አደጋ ቢደርስበት፥ ሽበቴን በመሪር ኀዘን ወደ መቃብር ታወርዱታላችሁ” አላቸው።


አንዱ በወጣበት በመቅረቱ፥ “በእርግጥ የአውሬ እራት ሆኖአል” አልሁ፤ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ይኸው የውሃ ሽታ ሆኖ ቀርቶአል።


እነርሱም ከግብጽ አገርም ወጡ፥ ወደ ከነዓንም ምድር ከአባታቸው ከያዕቆብ ዘንድ ደረሱ።


እስራኤልም ዮሴፍን፦ “ፊትህን አያለሁ ብዬ አላሰብሁም ነበር፥ እነሆም እግዚአብሔር ዘርህን ደግሞ አሳየኝ” አለው።


እነርሱ ባልታመኑ ጊዜ ሳቅሁላቸው፥ የፊቴም ብርሃን አበረታታቸው።


ብጠራው እርሱም ቢመልስልኝ ኖሮ፥ ቃሌን ሰማ ብዬ አላምንም ነበር።


የቤቱ ጌታ፥ የንብረቱ ሁሉ ገዢ አደረገው፥


የዕርገት መዝሙር። ጌታ የጽዮንን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፥ ሕልም የምናይ መስሎን ነበር።


ወደ ተራሮች መሠረት ወረድሁ፥ የምድር መወርወሪያዎችዋ ለዘለዓለም ተዘጉብኝ፤ ጌታ አምላኬ ሆይ አንተ ግን ሕይወቴን ከጉድጓድ አወጣሃት።


ነገር ግን ይህ ቃል ቅዠት መስሎ ታያቸውና አላመኑአቸውም።


እነርሱም “ጌታ በእርግጥ ተነሥቷል፥ ለስምዖንም ታይቷል” ይሉ ነበር።


እነርሱም ከደስታ ብዛት ገና ሳያምኑ ገና በመገረም ላይ ሳሉ “በዚህ አንዳች የሚበላ ነገር አላችሁን?” አላቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos