ዘፍጥረት 44:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይሁዳም ወደ ዮሴፍ ቀረብ ብሎ፥ “ጌታዬ ሆይ፤ እኔ አገልጋይህ አንዲት ቃል ብቻ ልናገር፤ አንተም የፈርዖን ያህል የተከበርህ ስለሆንህ፥ እባክህን እኔን አገልጋይህን አትቈጣኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁዳም ወደ ዮሴፍ ቀረብ ብሎ፣ “ጌታዬ ሆይ፤ እኔ አገልጋይህ አንዲት ቃል ብቻ ልናገር፤ አንተም የፈርዖንን ያህል የተከበርህ ስለ ሆንህ፣ እባክህን እኔን አገልጋይህን አትቈጣኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይሁዳ ወደ ዮሴፍ ቀርቦ እንዲህ አለ፤ “ጌታዬ ሆይ፤ እባክህ አንድ ቃል እንድናገር ፍቀድልኝ፤ ምንም እንኳ የፈርዖንን ያኽል የተከበርክ ብትሆን እባክህ አትቈጣኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይሁዳም ወደ እርሱ ቀረበ፤ እንዲህም አለ፥ “ጌታዬ ሆይ፥ እኔ አገልጋይህ በፊትህ አንዲት ቃልን እንድናገር እለምናለሁ፤ እኔን አገልጋይህን አትቈጣኝ፤ አንተ ከፈርዖን ቀጥለህ ነህና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይሁዳም ወደ እርሱ ቀረበ እንዲህም አለ፦ ጌታዬ ሆይ እኔ ባርያን በጌታዬ ጆሮ አንዲት ቃልን እንድናገር እለምናለሁ እኔንም ባሪያህን አትቆጣኝ አንተ እንደ ፈርዖን ነህና። |
እርሱም፦ “እኔ ደግሞ አንድ ጊዜ ብቻ ብናገር ጌታዬ አይቆጣ፥ ምናልባት ከዚያ ዐሥር ቢገኙሳ?” አለ። እርሱም፦ “ስለ አሥሩ አላጠፋትም” አለ።
እነሆ እኛ በእርሻ መካከል ነዶ ስናስር ነበር፥ እነሆም፥ የእኔ ነዶ ቀጥ ብላ ቆመች፥ የእናንተም ነዶች በዙሪያ ከብበው እነሆ ለእኔ ነዶ ሰገዱ።”
ከዚህ በኋላ ፈርዖን ዮሴፍን፥ “እኔ ፈርዖን ነኝ፤ ሆኖም በመላዪቱ ግብጽ ያላንተ ትእዛዝ እጁንም ሆነ እግሩን ልውስ የሚያደርግ አይኖርም” አለው።
ዮሴፍም፥ “ይህንንስ ፈጽሞ አላደርገውም፤ ባርያዬ የሚሆነው ጽዋው የተገኘበት ሰው ብቻ ነው፤ የቀራችሁት በሰላም ወደ አባታችሁ ተመለሱ” አላቸው።
ወንድሞች ሆይ! ስለ አባቶች አለቃ ስለ ዳዊት እንደ ሞተም እንደ ተቀበረም ለእናንተ በግልጥ እናገር ዘንድ ፍቀዱልኝ፤ መቃብሩም እስከ ዛሬ በእኛ ዘንድ ነው።