ሌላውን ወንድማችሁንና ብንያምን ይዛችሁ ለመመለስ እንድትችሉ ሁሉን የሚችል አምላክ በምሕረቱ የዚያን ሰው ልብ ያራራላችሁ። እንግዲህ ልጆቼንም ባጣ ምን አደርጋለሁ፤ ያመጣውን እቀበላለሁ።”
ዘፍጥረት 44:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም አዛዡ ፍተሻውን ከታላቁ ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ቀጠለ። በመጨረሻም፥ ጽዋው በብንያም ስልቻ ውስጥ ተገኘ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም አዛዡ ፍተሻውን ከታላቁ ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ቀጠለ። በመጨረሻም፣ ጽዋው በብንያም ስልቻ ውስጥ ተገኘ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዮሴፍ አገልጋይ ከታላቁ ጀምሮ እስከ ታናሹ የሁሉንም ስልቻ በተራ በመበርበር ዋንጫውን በጥንቃቄ ፈለገ፤ በመጨረሻ ግን ዋንጫው በብንያም ስልቻ ውስጥ ተገኘ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም ከታላቁ ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ በረበራቸው፤ ጽዋውንም በብንያም ዓይበት ውስጥ አገኘው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም ከታላቁ ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ በረበራቸው ጽዋውንም በብንያም ዓይበት ውስጥ አገኘው። |
ሌላውን ወንድማችሁንና ብንያምን ይዛችሁ ለመመለስ እንድትችሉ ሁሉን የሚችል አምላክ በምሕረቱ የዚያን ሰው ልብ ያራራላችሁ። እንግዲህ ልጆቼንም ባጣ ምን አደርጋለሁ፤ ያመጣውን እቀበላለሁ።”