ዮሴፍም ወንድሞቹን ገና ሲያያቸው ወዲያውኑ ዐወቃቸው፤ ነገር ግን እንደማያውቃቸው ሆኖ፥ “ከየት የመጣችሁ ናችሁ?” ብሎ በቁጣ ቃል ተናገራቸው። እነርሱም፥ “እህል፤ ለመሸመት ከከነዓን ምድር የመጣን ነን” ብለው መለሱለት።
ዘፍጥረት 43:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንድማማቾቹ ከበኩሩ እስከ ታናሹ እንደየዕድሜአቸው በዮሴፍ ፊት በተርታ ተቀምጠው ነበር፤ በመገረምም እርስ በርሳቸው ተያዩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወንድማማቾቹ ከበኵሩ እስከ ታናሹ እንደየዕድሜያቸው በዮሴፍ ፊት በተርታ ተቀምጠው ነበር፤ በመገረምም እርስ በርሳቸው ተያዩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወንድማማቾቹ ከታላቁ አንሥቶ እስከ ታናሹ በዕድሜ ተራ በዮሴፍ ፊት ለፊት ተቀመጡ፤ እንዴት እንደ ተቀመጡ ባዩ ጊዜ በመደነቅ እርስ በርሳቸው ተያዩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በፊቱም በኵሩ እንደ ታላቅነቱ፥ ታናሹም እንደ ታናሽነቱ ተቀመጡ፤ እነርሱም እርስ በርሳቸው በመደነቅ ተያዩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በፊቱም በኵሩ እንደ ታላቅነቱ ታናሹም እንደ ታናሽነቱ ተቀመጡ ሰዎቹም እርስ በርሳቸው ተደነቁ። |
ዮሴፍም ወንድሞቹን ገና ሲያያቸው ወዲያውኑ ዐወቃቸው፤ ነገር ግን እንደማያውቃቸው ሆኖ፥ “ከየት የመጣችሁ ናችሁ?” ብሎ በቁጣ ቃል ተናገራቸው። እነርሱም፥ “እህል፤ ለመሸመት ከከነዓን ምድር የመጣን ነን” ብለው መለሱለት።
ኢየሱስም ሰምቶ ተደነቀና ይከተሉት የነበሩትን እንዲህ አላቸው “እውነት እላችኋለሁ፤ በእስራኤል እንኳ እንዲህ ያለ ትልቅ እምነት አላገኘሁም።