Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፍጥረት 48:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ዮሴፍም አባቱን፦ “አባቴ ሆይ እንዲህ አይደለም፥ በኩሩ ይህ ነውና፥ ቀኝህን በራሱ ላይ አድርግ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ዮሴፍም፣ “አባቴ ሆይ፤ እንዲህ አይደለም፤ በኵሩ ይህኛው ስለ ሆነ፣ ቀኝ እጅህን እርሱ ራስ ላይ አድርግ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 “አባቴ ሆይ፥ እንደዚህ አይደለም፤ በኲሩ ይህኛው ስለ ሆነ ቀኝ እጅህን በእርሱ ራስ ላይ አኑር” አለው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ዮሴ​ፍም አባ​ቱን፥ “አባቴ ሆይ፥ እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ በኵሩ ይህ ነውና ቀኝ​ህን በራሱ ላይ አድ​ርግ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ዮሴፍም አባቱን፦ አባቴ ሆይ እንዲህ አይደለም፥ በኵሩ ይህ ነውና ቀኝህን በራሱ ላይ አድርግ አለው።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 48:18
11 Referencias Cruzadas  

እኔም ‘ጌታ ሆይ! አይሆንም፤ ርኩስ ወይም የሚያስጸይፍ ከቶ ወደ አፌ ገብቶ አያውቅምና፤’ አልሁ።


ጴጥሮስ ግን “ጌታ ሆይ! አይሆንም፤ አንዳች ርኩስ የሚያስጸይፍም ከቶ በልቼ አላውቅምና፤” አለ።


ብልሆቹ ግን ‘ለእኛና ለእናንተ ላይበቃ ይችላል፤ ይልቅስ ወደሚሸጡት ሄዳችሁ ለራሳችሁ ግዙ’ ሲሉ መለሱላቸው።


እንዲህ አይሆንም፤ እናንተ ወንዶቹ ሂዱና ጌታን አገልግሉ፥ የጠየቃችሁት ይህንን ነውና።” ከፈርዖንም ፊት አባረሩአቸው።


ሮቤል፥ አንተ በኩር ልጄና ኃይሌ፥ የጉብዝናዬም መጀመሪያ፥ የክብር አለቃና የኃይል አለቃ።


ወንድማማቾቹ ከበኩሩ እስከ ታናሹ እንደየዕድሜአቸው በዮሴፍ ፊት በተርታ ተቀምጠው ነበር፤ በመገረምም እርስ በርሳቸው ተያዩ።


ላባም እንዲህ አለ፦ “በአገራችን ታላቂቱ ሳለች፥ ታናሺቱን እንስጥ ዘንድ ወግ አይደለም፥


ርብቃም ከእርሷ ዘንድ በቤት የነበረችውን የታላቁን ልጇን የዔሳውን መልካሙን ልብስ አመጣች፥ ታናሹን ልጇን ያዕቆብንም አለበሰችው፥


ሎጥም፥ አላቸው፦ “ጌቶቼ ሆይ፥ እንዲህስ አይሁን፥


ዮሴፍም አባቱ ቀኝ እጁን በኤፍሬም ራስ ላይ ጭኖ ባየ ጊዜ አሳዘነው፥ የአባቱንም እጅ በምናሴ ራስ ላይ ይጭነው ዘንድ ከኤፍሬም ራስ ላይ አነሣው።


አባቱም እንዲህ ሲል እንቢታውን ገለጸ፦ “አውቄአለሁ ልጄ ሆይ፥ አውቄአለሁ፥ ይህም ደግሞ ሕዝብ ይሆናል ታላቅም ይሆናል፥ ነገር ግን ታናሽ ወንድሙ ከእርሱ ይበልጣል፥ ዘሩም የአሕዛብ ሙላት ይሆናል።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios