እርሱም፦ “ሄደህ ወንድሞችህና በጎቹ ደኅና እንደ ሆኑ እይ፥ ወሬአቸውንም አምጣልኝ” አለው። በዚህ ዓይነት ከኬብሮን ሸለቆ ላከው፥ ወደ ሴኬምም መጣ።
ዘፍጥረት 43:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮሴፍም ስለ ደኅንነታቸው ጠየቃቸው፤ ከዚያም “ሽማግሌ አባት እንዳላችሁ ነግራችሁኝ ነበር፤ ደኅና ነው? አሁንም በሕይወት አለ?” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮሴፍም ስለ ደኅንነታቸው ጠየቃቸው፤ ከዚያም “ሽማግሌ አባት እንዳላችሁ ነግራችሁኝ ነበር፤ ደኅና ነው? አሁንም በሕይወት አለ?” አላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም ስለ ደኅንነታቸው ከጠየቃቸው በኋላ “ያ የነገራችሁኝ ሽማግሌ አባታችሁ እንዴት ነው? አሁንም በሕይወት አለን?” አላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም ደኅንነታቸውን ጠየቃቸው፤ እንዲህም አለ፥ “የነገራችሁኝ ሽማግሌ አባታችሁ ደኅና ነውን? ገና በሕይወት አለን?” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም ደኅንነታቸውን ጠየቃቸው እንዲህም አለ፦ የነገራችሁኝ ሽማግሌ አባታችሁ ደኅና ነውን? ገና በሕይወት አለን? |
እርሱም፦ “ሄደህ ወንድሞችህና በጎቹ ደኅና እንደ ሆኑ እይ፥ ወሬአቸውንም አምጣልኝ” አለው። በዚህ ዓይነት ከኬብሮን ሸለቆ ላከው፥ ወደ ሴኬምም መጣ።
እነርሱ ግን መልሰው፥ “እኛ አገልጋዮችህ በከነዓን አገር ከሚኖር ከአንድ ሰው የተወለድን ዐሥራ ሁለት ወንድማማቾች ነን። ትንሹ ወንድማችን አባታችን ዘንድ ሲሆን፥ አንዱ ግን የለም” አሉት።
እነርሱም፥ “ሰውየው ስለ ራሳችንና ስለ ቤተሰባችን አጥብቆ ጠየቀን፤ እንደገናም ‘አባታችሁ አሁንም በሕይወት አለ? ሌላስ ወንድም አላችሁ’ ሲል ጠየቀን። እኛም ለጥያቄው መልስ ሰጠነው። ታድያ፥ ‘ወንድማችሁን ይዛችሁ ወደዚህ እንድትመጡ’ እንደሚል እንዴት ማወቅ እንችል ነበር?” ብለው መለሱለት።
ዮሴፍም ለወንድሞቹ “እኔ ዮሴፍ ነኝ፥ አባቴ እስከ አሁን በሕይወቱ አለን?” አለ። ወንድሞቹም፥ በፊቱ ደንግጠው ነበርና፥ ሊመልሱለት አልቻሉም።
ቶዑም ከአድርአዛር ጋር ሁልጊዜ ይዋጋ ነበርና ዳዊት አድርአዛርን ወግቶ ድል ስለ አደረገው ደኅንነቱን እንዲጠይቀውና እንዲመርቀው ልጁን አዶራምን ወደ ዳዊት ላከው፤ እርሱም የወርቅና የብር የናስም ዕቃ ይዞ መጣ።