La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 41:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የቀጨጩት የእሸት ዛላዎች፥ ፍሬያቸው የተንዠረገገውን ሰባቱን ያማሩ ዛላዎች ዋጡአቸው። በዚህ ጊዜ ፈርዖን ከእንቅልፉ ነቃ፤ ነገሩ ሕልም ነበር።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የቀጨጩት የእሸት ዛላዎች፣ ፍሬአቸው የተንዠረገገውን ሰባቱን ያማሩ ዛላዎች ዋጧቸው። በዚህ ጊዜ ፈርዖን ከእንቅልፉ ነቃ፤ ነገሩ ሕልም ነበር።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሰባቱም የቀጨጩ የእሸት ዛላዎች፥ ሰባቱን የዳበሩና ያማሩ የእሸት ዛላዎች ዋጡአቸው፤ ንጉሡም ከእንቅልፉ በነቃ ጊዜ ሕልም ማየቱን ተገነዘበ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እነ​ዚ​ያም የሰ​ለ​ቱና ነፋስ የመ​ታ​ቸው እሸ​ቶች ሰባ​ቱን ያማ​ሩና የጐ​መሩ እሸ​ቶች ዋጡ​አ​ቸው። ፈር​ዖ​ንም ነቃ፤ እነ​ሆም ሕልም ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የሰለቱትም እሽቶች ስባቱን ያማሩና የዳበሩ እሸቶች ዋጡአቸው።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 41:7
5 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔርም ሌሊት በሕልም ወደ አቢሜሌክ መጣ፥ “እነሆ፥ አንተ ስለ ወሰድሃት ሴት ትሞታለህ፤ እርሷ ባለ ባል ናትና” አለው።


ዮሴፍም ሕልምን አለመ፥ ለወንድሞቹም ነገራቸው፥ እነርሱም እንደገና አብዝተው ጠሉት።


ከዚያም የቀጨጩና በምሥራቅ ነፋስ ተመትተው የደረቁ ሰባት የእሸት ዛላዎች ወጡ።


በነጋታውም ፈርዖን መንፈሱ ታወከበት፤ ስለዚህ በግብጽ አገር ያሉትን አስማተኞችና ጥበበኞች በሙሉ አስጠርቶ ሕልሞቹን ነገራቸው፥ ይሁን እንጂ ሕልሞቹን ሊተረጉምለት የቻለ አንድም ሰው አልተገኘም።


ሰሎሞን ከእንቅልፉ በነቃ ጊዜ እግዚአብሔር በሕልም ተገልጦ ያነጋገረው መሆኑን ተገነዘበ፤ ከዚህ በኋላ ሰሎሞን ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሶ ሄደ፤ በጌታ የቃል ኪዳን ታቦት ፊት ቆሞ የሚቃጠል መሥዋዕትንና የኅብረት መሥዋዕት አቀረበ፤ ለባለሟሎቹም ሁሉ ግብዣ አደረገ።