Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 41:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ሰባቱም የቀጨጩ የእሸት ዛላዎች፥ ሰባቱን የዳበሩና ያማሩ የእሸት ዛላዎች ዋጡአቸው፤ ንጉሡም ከእንቅልፉ በነቃ ጊዜ ሕልም ማየቱን ተገነዘበ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 የቀጨጩት የእሸት ዛላዎች፣ ፍሬአቸው የተንዠረገገውን ሰባቱን ያማሩ ዛላዎች ዋጧቸው። በዚህ ጊዜ ፈርዖን ከእንቅልፉ ነቃ፤ ነገሩ ሕልም ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 የቀጨጩት የእሸት ዛላዎች፥ ፍሬያቸው የተንዠረገገውን ሰባቱን ያማሩ ዛላዎች ዋጡአቸው። በዚህ ጊዜ ፈርዖን ከእንቅልፉ ነቃ፤ ነገሩ ሕልም ነበር።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 እነ​ዚ​ያም የሰ​ለ​ቱና ነፋስ የመ​ታ​ቸው እሸ​ቶች ሰባ​ቱን ያማ​ሩና የጐ​መሩ እሸ​ቶች ዋጡ​አ​ቸው። ፈር​ዖ​ንም ነቃ፤ እነ​ሆም ሕልም ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 የሰለቱትም እሽቶች ስባቱን ያማሩና የዳበሩ እሸቶች ዋጡአቸው።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 41:7
5 Referencias Cruzadas  

ነገር ግን አንድ ሌሊት እግዚአብሔር በሕልም ተገልጦ አቤሜሌክን “ይህች ሴት ባለባል ስለ ሆነች እርስዋን በመውሰድህ ምክንያት ትሞታለህ” አለው።


አንድ ሌሊት ዮሴፍ ሕልም አየ፤ ሕልሙን ለወንድሞቹ በነገራቸውም ጊዜ ከቀድሞው ይበልጥ ጠሉት።


ቀጥሎም የቀጨጩና ከበረሓ በተነሣ የምሥራቅ ነፋስ ተመተው የሰለቱ ሰባት የእሸት ዛላዎች በቅለው አየ።


ጠዋት ከመኝታው ሲነሣ መንፈሱ ታወከ፤ ስለዚህ በግብጽ ምድር ያሉትን አስማተኞችና ጥበበኞች ሁሉ አስጠርቶ ሕልሙን ነገራቸው፤ ነገር ግን የሕልሞቹን ትርጒም ለመግለጥ የቻለ አንድ እንኳ አልነበረም።


ሰሎሞን ከእንቅልፉ በነቃ ጊዜ እግዚአብሔር በሕልም ተገልጦ ያነጋገረው መሆኑን ተገነዘበ፤ ከዚህ በኋላ ሰሎሞን ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሶ ሄደ፤ በእግዚአብሔርም የቃል ኪዳን ታቦት ፊት ቆሞ የሚቃጠል መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቀረበ፤ ከዚህም በኋላ ባለሟሎቹ ለሆኑ ባለሥልጣኖች ሁሉ ግብዣ አደረገ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos