ዘፍጥረት 36:34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮባብም ሞተ፥ በስፍራውም የቴማኒው አገር ሑሻም ነገሠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢዮባብ ሲሞት፣ የቴማን አገር ሰው ሑሳም በምትኩ ነገሠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮባብም በሞተ ጊዜ የቴማን አገር ተወላጅ ሑሻም በእርሱ እግር ተተክቶ ነገሠ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮባብም ሞተ፤ በእርሱም ፈንታ የቴማኒው ሀገር ሑሳም ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በስፍራውም የቴማኒው አገር ሑሳም ነገሠ |
ሦስቱ የኢዮብ ወዳጆች ይህን የደረሰበትን ክፉ ነገር ሁሉ ሰምተው ከየአገራቸው መጡ፥ እነርሱም ቴማናዊው ኤልፋዝ፥ ሹሐዊው ቢልዳድ፥ ነዕማታዊው ሶፋር ነበሩ። እነርሱም ሊያዝኑለትና ሊያጽናኑት በአንድነት ወደ እርሱ ለመምጣት ተስማሙ።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በኤዶምያስ ላይ እጄን እዘረጋለሁ፥ ከእርሷም ሰውንና እንስሳን አጠፋለሁ፤ ባድማ አደርጋታለሁ፤ ከቴማን ጀምሮ እስከ ድዳን ድረስ በሰይፍ ይወድቃሉ።