ዘፍጥረት 36:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዲሾን አለቃ፥ ኤጽር አለቃ፥ ዲሻን አለቃ፥ በሴይር ምድር አለቆች የሆኑ የሖሪ አለቆቹ እነዚህ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዲሶን፣ ኤጽርና ዲሳን። እነዚህ በሴይር ምድር እንደየነገዳቸው የሖሪውያን የነገድ አለቆች ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዲሾን፥ ኤጼር፥ ዲሻን፤ እነዚህ ሁሉ በኤዶም ምድር አለቆች የሆኑ የሖሪው ዘሮች ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዲሶን መስፍን፥ ኤሶር መስፍን፥ ሪሶን መስፍን፤ በሴይር ምድር በየሹመታቸው መሳፍንት የሆኑ የሖሪ መሳፍንት እነዚህ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዓና አለቃ፥ ዲሶን አለቃ፥ ኤጽር አለቃ ዲሳን አለቆቹ፤ በሴይር ምድር አለቆች የሆኑ የሖሪ አለቆቹ እነዚህ ናቸው። |
ከዚህም በኋላ እርሱ፥ የጦር አለቆች፥ የንጉሡ ክብር ዘብና የቤተ መንግሥቱ ዘብ ጠባቂዎች ንጉሡን ከቤተ መቅደስ እስከ ቤተ መንግሥት አጅበው እንዲሄዱና ሕዝቡም ሁሉ ከኋላ እንዲከተል አደረገ፤ ኢዮአስም በዘብ ጠባቂዎች ቅጽር በር በኩል ገብቶ በዙፋኑ ላይ ተቀመጠ።
በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ጢሮስ እንደ አንድ ንጉሥ ዘመን ሰባ ዓመት ያህል የተረሳች ትሆናለች፤ ከሰባ ዓመት በኋላ ግን ለጢሮስ በጋለሞታ ዘፈን እንደሚሆን እንዲሁ ይሆናል።