ዘፍጥረት 36:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዔሳው ሚስት የኦሆሊባማ ልጆች እነዚህ ናቸው፦ የዑሽ አለቃ፥ ያዕላም አለቃ፥ ቆሬ አለቃ፥ የዔሳው ሚስት የዓና ልጅ የኦሆሊባማ አለቆች እነዚህ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዔሳው ሚስት የአህሊባም ልጆች፦ አለቃ የዑስ፣ አለቃ የዕላምና፣ አለቃ ቆሬ፤ እነዚህ ከዓና ልጅ፣ ከዔሳው ሚስት ከኦሆሊባማ የተገኙ የነገድ አለቆች ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዔሳው ሚስት ከኦሆሊባማ የተወለዱት የነገድ አለቆች፦ የዑሽ፥ ያዕላምና ቆሬ ናቸው፤ እነዚህ ከዐና ልጅ ከኦሆሊባማ የተወለዱ የዔሳው ትውልድ የነገድ አለቆች ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዔሳው ሚስት የኤሌባማ ልጆች መሳፍንት እነዚህ ናቸው፤ ዮሔል መስፍን፥ ይጉሜል መስፍን፥ ቆሬ መስፍን፤ የዔሳው ሚስት የሐና ልጅ የኤሌባማ ልጆች መሳፍንት እነዚህ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዔሳው ሚስት የአህሊባማ ልጆች እነዚህ ናቸው የዑስ አለቃ የዕላማ አለቃ ቆሬ አለቃ የዔሳው ሚስት የዓን ልጅ የአህሊባማ አለቆአ እነዚህ ናቸው። |
የዔሳው ልጅ የረዑኤል ልጆች እነዚህ ናቸው፥ ናሐት አለቃ፥ ዘራሕ አለቃ፥ ሻማ አለቃ፥ ሚዛህ አለቃ፥ በኤዶም ምድር የረዑኤል ልጆች አለቆች እነዚህ ናቸው፤ እነዚህም የዔሳው ሚስት የባሴማት ልጆች ናቸው።