Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 36:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 የዔሳው ሚስት የአህሊባም ልጆች፦ አለቃ የዑስ፣ አለቃ የዕላምና፣ አለቃ ቆሬ፤ እነዚህ ከዓና ልጅ፣ ከዔሳው ሚስት ከኦሆሊባማ የተገኙ የነገድ አለቆች ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 የዔሳው ሚስት የኦሆሊባማ ልጆች እነዚህ ናቸው፦ የዑሽ አለቃ፥ ያዕላም አለቃ፥ ቆሬ አለቃ፥ የዔሳው ሚስት የዓና ልጅ የኦሆሊባማ አለቆች እነዚህ ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ከዔሳው ሚስት ከኦሆሊባማ የተወለዱት የነገድ አለቆች፦ የዑሽ፥ ያዕላምና ቆሬ ናቸው፤ እነዚህ ከዐና ልጅ ከኦሆሊባማ የተወለዱ የዔሳው ትውልድ የነገድ አለቆች ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 የዔ​ሳው ሚስት የኤ​ሌ​ባማ ልጆች መሳ​ፍ​ንት እነ​ዚህ ናቸው፤ ዮሔል መስ​ፍን፥ ይጉ​ሜል መስ​ፍን፥ ቆሬ መስ​ፍን፤ የዔ​ሳው ሚስት የሐና ልጅ የኤ​ሌ​ባማ ልጆች መሳ​ፍ​ንት እነ​ዚህ ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 የዔሳው ሚስት የአህሊባማ ልጆች እነዚህ ናቸው የዑስ አለቃ የዕላማ አለቃ ቆሬ አለቃ የዔሳው ሚስት የዓን ልጅ የአህሊባማ አለቆአ እነዚህ ናቸው።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 36:18
6 Referencias Cruzadas  

የፂብዖን የልጅ ልጅ፣ የዓና ልጅ የዔሳው ሚስት ኦሆሊባማ ለዔሳው የወለደቻቸው ልጆች፦ የዑስ፣ የዕላምና ቆሬ።


የዔሳው ልጅ ራጉኤል ልጆች፦ አለቃ ናሖት፣ አለቃ ዛራ፣ አለቃ ሣማና አለቃ ሚዛህ፤ እነዚህ በኤዶም ምድር ከራጉኤል የተገኙ የነገድ አለቆች፣ የዔሳው ሚስት የቤሴሞት የልጅ ልጅ ነበሩ።


እነዚህም ኤዶም የተባለው የዔሳው ልጆችና የነገድ አለቆቻቸው ነበሩ።


ዔሳው ከከነዓን ሴቶች አገባ፤ እነርሱም፦ የኬጢያዊው የኤሎን ልጅ ዓዳን፣ የኤዊያዊው የፂብዖን ልጅ ዓና የወለዳት ኦሆሊባማ፣


እንደዚሁም ኦሆሊባማ የዑስን፣ የዕላምንና ቆሬን ወለደችለት፤ እነዚህ ዔሳው በከነዓን አገር የወለዳቸው ልጆች ናቸው።


የዔሳው ወንዶች ልጆች፤ ኤልፋዝ፣ ራጉኤል፣ የዑስ፣ የዕላም፣ ቆሬ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos