ዘፍጥረት 35:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይስሐቅም ነፍሱን ሰጠ፥ ሞተም፥ ሸምግሎ ዕድሜንም ጠግቦ ወደ ወገኖቹ ተከማቸ፥ ልጆቹም ዔሳውና ያዕቆብ ቀበሩት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሥሐቅም አርጅቶ፣ ዕድሜ ጠግቦ ሞተ፤ ወደ ወገኖቹ ተሰበሰበ፤ ልጆቹም ዔሳውና ያዕቆብ ቀበሩት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዕድሜ ጠግቦ ካረጀ በኋላ ሞተ፤ ልጆቹም ዔሳውና ያዕቆብ ቀበሩት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይስሐቅም ሸምግሎ ዕድሜንም ጠግቦ ሞተ፤ ወደ ወገኖቹም ተጨመረ፤ ልጆቹም ዔሳውና ያዕቆብ ቀበሩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይስሐቅም ነፍሱን ሰጠም፥ ሞተም ሸምግሎ ዕድሜንም ጠግቦ ወደ ወገኖቹ ተከማቸ፤ ልጆቹም ዔሳውና ያዕቆብ ቀበሩት። |
ዔሳውም አባቱ ስለ ባረከው በያዕቆብ ቂም ያዘበት፥ ዔሳውም በልቡ አለ፦ “ለአባቴ የልቅሶ ቀን ቀርቦአል፥ ከዚያም በኋላ ወንድሜን ያዕቆብን እገድለዋለሁ።”
ወንዶች ልጆቹና ሴቶች ልጆቹም ሁሉ ሊያጽናኑት ተነሡ፥ መጽናናትን እንቢ አለ፥ እንዲህም አለ፦ “ወደ ልጄ ወደ ሙታን ስፍራ እያዘንሁ እወርዳለሁ።” አባቱም እንደዚህ ስለ እርሱ አለቀሰ።