ዘፍጥረት 35:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስራኤልም ከዚያ ተነሣ፥ ድንኳኑንም ከዔዴር ግንብ ባሻገር ተከለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤልም ጕዞውን በመቀጠል ከጋዴር ወንዝ ባሻገር ድንኳኑን ተከለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያዕቆብ ጒዞውን ቀጥሎ በዔዴር ግንብ ባሻገር ድንኳን ተክሎ ሰፈረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህም በኋላ እስራኤል በዚያች ምድር ሳለ ሮቤል ሄደ፤ ከአባቱ ከያዕቆብ ዕቅብት ከባላ ጋርም ተኛ፤ እስራኤልም ሰማ። በፊቱም ክፉ ነገር ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስራኤልም ከዚያ ተነሣ ድንኳኑንም ከጋዴር ግንብ በስተ ወዲያ ተከለ። |
በደቡብም በኩል በምድራቸው ዳርቻ አጠገብ እስከ ኤዶምያስ ድንበር ያሉት የይሁዳ ልጆች ነገድ ከተሞች እነዚህ ነበሩ፤ ቀብሴኤል፥ ዔደር፥ ያጉር፥