በእውነት መባረክን እባርክሃለሁ፥ ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብት እና በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ አበዛዋለሁ፤ ዘሮችህም የጠላቶችን ደጅ ይወርሳሉ፥
ዘፍጥረት 34:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤሞርና ሴኬም ልጁም ወደ ከተማቸው አደባባይ ገቡ፥ ለከተማቸውም ሰዎች እንዲህ ብለው ነገሩ፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ኤሞርና ልጁ ሴኬም ይህንኑ ለወገኖቻቸው ለመንገር ወደ ከተማቸው በር ሄዱ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ሐሞርና ልጁ ሴኬም በከተማው በር አጠገብ ወዳለው መሰብሰቢያ ቦታ ሄዱ፤ ለከተማይቱ ነዋሪዎች እንዲህ በማለት ንግግር አደረጉ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤሞርና ልጁ ሴኬምም ሄዱና ወደ ከተማቸው በር ደረሱ፤ ለከተማቸውም ሰዎች ሁሉ እንዲህ ብለው ነገሩ፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤሞርና ሴኬም ልጁም ወደ ከተማቸው አደባባይ ገቡ ለከተማቸውም ሰዎች እንዲህ ብለው |
በእውነት መባረክን እባርክሃለሁ፥ ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብት እና በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ አበዛዋለሁ፤ ዘሮችህም የጠላቶችን ደጅ ይወርሳሉ፥
ኤፍሮንም በኬጢ ልጆች መካከል ተቀምጦ ነበር፥ የኬጢ ሰው ኤፍሮንም የኬጢ ልጆችና ወደ ከተማ የሚገቡ ሁሉ ሲሰሙ ለአብርሃም እንዲህ ሲል መለሰለት፦
“እነዚህ ሰዎች በእኛ ዘንድ የሰላም ሰዎች ናቸው፥ በምድራችን ይቀመጡ፥ ይነግዱባትም፥ እነሆም ምድሪቱ ሰፊ ናት፥ ሴቶች ልጆቻቸውን እንውሰድ፥ ለእነርሱም ሴቶች ልጆቻችንን እንስጥ።
አቤሴሎምም በማለዳ ተነሥቶ ወደ ከተማዪቱ መግቢያ በር በሚወስደው መንገድ ዳር ይቆም ነበር። ማናቸውም ባለ ጉዳይ አቤቱታውን ለንጉሡ አቅርቦ ለማስወሰን በሚመጣበት ጊዜ ሁሉ፥ አቤሴሎም ወደ እርሱ እየጠራ፥ “አንተ ከየትኛው ከተማ ነው የመጣኸው?” በማለት ይጠይቀዋል፤ ያም ሰው፥ “አገልጋይህ ከእስራኤል ነገዶች ከአንዱ ነው” ብሎ ይመልስለታል።
ጻድቁን የምታሠቃዩ፥ ጉቦንም የምትቀበሉ፥ በበሩም አደባባይ የችግረኛውን ፍርድ የምታጣምሙ እናንተ ሆይ! በደላችሁ እንዴት እንደ በዛ፥ ኃጢአታችሁም እንዴት እንደ ጸና እኔ አውቃለሁና።
ቦዔዝም ወደ ከተማይቱ በር አደባባይ ወጥቶ በዚያ ተቀመጠ። እነሆም፥ ከዚህ በፊት ቦዔዝ ስለ እርሱ የተናገረው የእርሱ የቅርብ ዘመድ ወደዚያው ቦታ መጣ፤ ቦዔዝም ጠርቶ፦ “ወዳጄ ሆይ! ቀረብ በልና አጠገቤ ተቀመጥ” አለው። እርሱም ቀረብ ብሎ ተቀመጠ።