ዘፍጥረት 32:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም የያዕቆብን ጭን ይዞ የወርቹን ሹልዳ ነክቶታልና፥ የእስራኤል ልጆች እስከ ዛሬ ድረስ የወርችን (በጭን መጋጠሚያ ላይ ያለውን) ሹልዳ አይበሉም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህም የተነሣ የእስራኤል ልጆች እስከ ዛሬ ድረስ ሹልዳን ከጭኑ ጋራ የሚያገናኘውን ሥጋ አይበሉም፤ ምክንያቱም በጭኑ መጋጠሚያ ላይ ያለው የያዕቆብ ሹልዳ ተነክቶ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያዕቆብ ከሰውየው ጋር ሲታገል ሰውየው ሹልዳውን መቶት ስለ ነበር እስራኤላውያን እስከ ዛሬ ድረስ በጭን መጋጠሚያ ላይ ያለውን የሹልዳ ሥጋ አይበሉም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህም የእስራኤል ልጆች እስከ ዛሬ ድረስ የወርችን ሹልዳ አይበሉም፤ የያዕቆብን ጭን ይዞ የወርቹን ሹልዳ አደንዝዞአልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህም የእስራኤል ልጆች እስከ ዛሬ ድረስ የወርችን ሹልዳ አይበሉም፤ የያዕቆብን ጭን ይዞ የወርችን ሹልዳ አደንዝዞአልን። |
ያዕቆብም ዓይኑን አነሣ ተመለከተም፥ እነሆም ዔሳው እየመጣ ነበር፥ ከእርሱም ጋር አራት መቶ ሰዎች ነበሩ። ልጆቹንም ከፍሎ ወደ ልያና ወደ ራሔል ወደ ሁለቱም አገልጋዮች አደረጋቸው።
የእስራኤል ንጉሥ ኢዮርብዓም በኮረብታማው በኤፍሬም አገር የምትገኘውን የሴኬምን ከተማ ምሽግ አድርጎ በዚያ ለጥቂት ጊዜ ቆየ፤ ከዚያም በመነሣት የፐኑኤልን ከተማ ምሽግ አድርጎ ሠራ፤
የዳጎን ካህናትም ሆኑ ሌሎች በአሽዶድ ወዳለው የዳጎን ቤት የሚገቡ ሁሉ እስከ ዛሬ ድረስ እግራቸው ደጃፉን እንዳይረግጥ ተራምደው የሚያልፉት በዚሁ ምክንያት ነው።