ዘፍጥረት 32:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚህንም መንጎቹ በየወገኑ ከፍሎ በአገልጋዮቹ እጅ አደረጋቸው፥ አገልጋዮቹንም፦ “ከእኔ ቀድማችሁ ሂዱ፥ በመንጋው እና መንጋው መካከልም እርቀት አኑሩ” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህንም በየመንጋው ለይቶ፣ የሚነዷቸውን ጠባቂዎች መደበላቸው፤ ጠባቂዎቹንም፣ “እናንተ ቀድማችሁኝ ሂዱ፣ መንጋዎቹንም አራርቃችሁ ንዷቸው” አላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚህንም በየመንጋው ከፈለና ለእያንዳንዳቸው እረኞች መደበላቸው፤ እረኞቹንም “ከእኔ ቀድማችሁ ሂዱ፤ በየመንጋው መካከል ርቀት እንዲኖር አድርጋችሁ፥ በመከታተል ሂዱ” አላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መንጎቹንም ለየብቻ ከፍሎ ለብላቴኖቹ ሰጣቸው፤ ብላቴኖቹንም፥ “በፊቴ እለፉ፤ መንጋውን ከመንጋው አርቁ” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መንጎቹን፥ በየወገኑ ከፍሎ በባሪያዎቹ እጅ አደረጋቸ ባሪያዎቹን፦ በፊቴ እለፉ መንጋውንና መንጋውንም አራርቁት አለ። |
የፊተኛውንም እንዲህ ብሎ አዘዘው፦ “ወንድሜ ዔሳው ያገኘህ እንደሆነ፥ ‘አንተ የማን ነህ? ወዴትስ ትሄዳለህ? በፊትህ ያለው ይህስ የማን ነው?’ ብሎ የጠየቀህም እንደሆነ፥
‘እንዲሁም ባርያህ ያዕቆብ ከኋላችን ነው’ እንድትሉት። እሱ ‘በፊቴ በሚሄደው እጅ መንሻ እታረቀዋለሁ፥ ከዚያም በኋላ ምናልባት ይቀበለኛል ፊቱንም አያለሁ’ ብሎ አስቧል።”