ዘፍጥረት 30:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ላባም፦ “በዓይንህ ፊት ሞገስን የማገኝ ብሆንስ ከዚህ ተቀመጥ፥ እግዚአብሔር በአንተ ምክንያት እንደ ባረከኝ ተመልክቼአለሁና” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ላባም እንዲህ አለው፤ “በጎ ፈቃድህ ቢሆን፣ እባክህ እዚሁ ከእኔ ጋራ ተቀመጥ፤ ምክንያቱም እግዚአብሔርም በአንተ ምክንያት እንደ ባረከኝ በንግርት ተረድቻለሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ላባም “በልዩ መገለጥ እንደ ተረዳሁት በአንተ ምክንያት እግዚአብሔር የባረከኝ መሆኑን እንድገልጽልህ ፍቀድልኝ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ላባም፥ “በዐይንህ ፊት ሞገስን የማገኝ ብሆንስ ከዚሁ ተቀመጥ፤ እግዚአብሔር በአንተ ምክንያት እንደ ባረከኝ ተመልክቼአለሁና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ላባም፦ በዓይንህ ፊት ሞገስን የማገኝ ብሆንስ ከዚህ ተቀመጥ፤ እግዚአብሔር በአንተ ምክንያት እንደ ባረከኝ ተመልክቼአለሁና አለው። |
በዚያችም ሌሊት ጌታ ተገለጠለት፥ እንዲህም አለው፦ “እኔ የአባትህ የአብርሃም አምላክ ነኝ፥ አትፍራ፥ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና፥ እባርክሃለሁ፥ ስለ ባርያዬ ስለ አብርሃም ዘርህን አበዛለሁ።”
ከእኔ መምጣት በፊት የነበረህ ጥቂት ነበርና፥ ዛሬም እጅግ በዛ፥ ወደ አንተ በመምጣቴም እግዚአብሔር ባረክህ፥ አሁንም እኔ ደግሞ ለቤቴ የምሠራው መቼ ነው?”
ዔሳውም፥ “ከእኔ ጋር ካሉት ሰዎች ከፍዬ ልተውልህን” አለ። እርሱ ግን፥ “ይህ ለምንድን ነው? በጌታዬ ዘንድ ሞገስን ማግኘት ይበቃኛል” አለ።
ጌታ ሆይ፥ ጆሮህ የባርያህን ጸሎት፥ ስምህን በመፍራት የሚደሰቱትን የባርያዎችህን ጸሎት ያድምጥ፤ ዛሬ ለባርያህ እባክህን አከናውንለት፥ በዚህም ሰው ፊት ሞገስን ስጠው። እኔም የንጉሡ ጠጅ አሳላፊ ነበርኩ።
ንጉሡንም፦ “ንጉሡን ደስ ቢያሰኘው፥ አገልጋይህም በፊትህ ሞገስ ቢያገኝ፥ መልሼ እንድሠራው የአባቶቼ መቃብር ወዳለበት ከተማ ወደ ይሁዳ እንድትልከኝ ነው” አልሁት።
እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለ፥ ፍሬውን በየጊዜው እንደሚሰጥ፥ ቅጠሉም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል፥ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል።
ከዐሥር አንድ ሰው እንኳን በምድሪቱ ቢቀር፤ እርሱም ደግሞ ይጠፋል፤ ነገር ግን የኮምበልና የባሉጥ ዛፍ በተቈረጠ ጊዜ ጉቶ እንደሚቀር፤ ቅዱሱም ዘር እንዲሁ በምድሪቱ ጉቶ ሆኖ ይቀራል።”
ጌታ እንዲህ ይላል፦ ወይን በዘለላው በተገኘች ጊዜ፥ “በረከት በእርሷ ላይ አለና አታጥፉት” እንደሚባለው፥ ሁሉን እንዳላጠፋ ስለ አገልጋዮቼ እንዲሁ አደርጋለሁ።
ሙሴም ጌታን እንዲህ አለው፦ “ለምን በባርያህ ላይ ክፉ አደረግህ? ለምንስ በፊትህ ሞገስ አላገኘሁም? ለምንስ የዚህን ሕዝብ ሁሉ ሸክም በእኔ ላይ አደረግህ?
እርሷም፦ “ጌታዬ ሆይ፥ ከአገልጋዮችህ እንደ አንዲቱ ሳልሆን አጽናንተኸኛልና፥ የባርያህንም ልብ ደስ አሰኝተሃልና በዓይንህ ሞገስ ላግኝ” አለችው።