Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 3:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 በግብፃውያንም ፊት ለዚህ ሕዝብ ሞገስን እሰጣለሁ፤ እንዲህም ይሆናል፥ በሄዳችሁ ጊዜ ባዶ እጃችሁን አትሄዱም፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 “ይህ ሕዝብ በግብጻውያን ዘንድ የመወደድን ጸጋ እንዲያገኝ ስለማደርግ በምትወጡበት ጊዜ ባዶ እጃችሁን አትሄዱም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 “በምትወጡበት ጊዜ ሕዝቡ በግብጻውያን ዘንድ ሞገስ እንዲያገኙ ስለማደርግ ባዶ እጃችሁን አትወጡም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 በግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንም ፊት ለዚህ ሕዝብ ሞገ​ስን እሰ​ጣ​ለሁ፤ በም​ት​ሄ​ዱም ጊዜ ባዶ እጃ​ች​ሁን አት​ሄ​ዱም፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 በግብፃውያንም ፊት ለዚህ ሕዝብ ሞገስን እሰጣለሁ፤ እንዲህም ይሆናል፤ በሄዳችሁ ጊዜ ባዶ እጃችሁን አትሄዱም፤

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 3:21
13 Referencias Cruzadas  

ጌታም ለሕዝቡ በግብፃውያን ፊት ሞገስን ሰጣቸው እነርሱም የፈለጉትን ሰጡአቸው። እነርሱም ግብጽን በዘበዙ።


ከወርቅና ከብርም ጋር አወጣቸው፥ በወገናቸውም ውስጥ የተደናቀፈ አልነበረም።


ጌታም ለሕዝቡ በግብፃውያን ፊት ሞገስን ሰጠ። ሙሴም በግብጽ ምድር፥ በፈርዖን አገልጋዮች ፊትና በሕዝቡ ፊት እጅግ ታላቅ ሰው ነበረ።


የሰው አካሄድ ጌታን ደስ ያሰኘው እንደሆነ፥ በእርሱና በጠላቶቹ መካከል ስንኳ ሰላምን ያደርጋል።


በማረኩአቸውም ሁሉ ፊት ሞገስን ሰጣቸው።


ይሁን እንጂ ዮሴፍ እዚያ እስር ቤት ባለበት ጊዜ ሁሉ፥ ጌታ ከእርሱ ጋር ነበረ፤ ቸርነቱንም አበዛለት፥ በወህኒ አዛዡም ዘንድ ሞገስን ሰጠው።


ከመከራውም ሁሉ አወጣው፤ በግብጽ ንጉሥ በፈርዖንም ፊት ሞገስንና ጥበብን ሰጠው፤ በግብጽና በቤቱ ሁሉ ላይም ቢትወደድ አድርጎ ሾመው።


ጌታ ሆይ፥ ጆሮህ የባርያህን ጸሎት፥ ስምህን በመፍራት የሚደሰቱትን የባርያዎችህን ጸሎት ያድምጥ፤ ዛሬ ለባርያህ እባክህን አከናውንለት፥ በዚህም ሰው ፊት ሞገስን ስጠው። እኔም የንጉሡ ጠጅ አሳላፊ ነበርኩ።


የእስራኤልም ልጆች እንደ ሙሴ ቃል አደረጉ፥ ከግብፃውያንም የብርንና የወርቅን ዕቃ ልብስንም ለመኑ።


ኃጢአታቸውንና አንተን ያሳዘኑበትን ዐመፅ ሁሉ ይቅር በል፤ ጠላቶቻቸውም እንዲራሩላቸው አድርግ፤


ደግሞም በባርነት በሚገዙአቸው ሕዝብ ላይ እኔ እፈርዳለሁ፥ ከዚያም በኋላ በብዙ ከብት ይወጣሉ።


ወንዱ ከጎረቤቱ ሴቲቱም ከጎረቤቷ የብር ዕቃና የወርቅ ዕቃ እንዲጠይቁ በሕዝቡ ጆሮ ተናገር።”


ነጻ በምታወጣው ጊዜ ባዶ እጁን አትስደደው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios