La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 27:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ይስሐቅም እጅግ ደነገጠ እንዲህም አለ፦ “ያደነውን አደን ወደ እኔ ያመጣ ማን ነው? አንተ ሳትመጣም ከሁሉ በላሁ ባረክሁትም፥ እርሱም የተባረከ ሆኖ ይኖራል።”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በዚህ ጊዜ ይሥሐቅ ክፉኛ እየተንቀጠቀጠ፣ “ታዲያ ቀደም ሲል ዐድኖ ያመጣልኝ ማን ነበር? አንተ ከመምጣትህ በፊት በልቼ መረቅሁት፤ እርሱም በርግጥ የተባረከ ይሆናል” አለው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ይስሐቅም እጅግ ደንግጦ እየተንቀጠቀጠ “ታዲያ፥ አውሬ አድኖ ያመጣልኝ ማን ነበር? ልክ አንተ ከመምጣትህ በፊት ተመገብኩ፤ የመጨረሻ ምርቃቴንም ሰጠሁት፤ ምርቃቱም የእርሱ ሆኖ ይኖራል” አለው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ይስ​ሐ​ቅም እጅግ ደነ​ገጠ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ያደ​ነ​ውን አደን ወደ እኔ ያመ​ጣው ማን ነው? አንተ ሳት​መ​ጣም ከሁሉ በላሁ፤ ባረ​ክ​ሁ​ትም፤ እር​ሱም የተ​ባ​ረከ ነው።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ይስሐቅም እጅግ ደነገጠ እንዲህም አለ፦ ያደነውን አደን ወደ እኔ ያመጣ ማን ነው? አንተ ሳትመጣም ከሁሉ በላሁ ባረክሁትም እርሱም የተባረከ ሆኖ ይኖራል።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 27:33
14 Referencias Cruzadas  

ጌታም እንዲህ አላት፥ “ሁለት ሕዝቦች በማሕፀንሽ አሉ፤ ሁለቱም ወገኖች ከውስጥሽ ተለያይተው ይወጣሉ፤ አንዱም ከሌላው ይበረታል፤ ታላቁም ለታናሹ አገልጋይ ይሆናል።”


እርሱም፦ “ወንድምህ በተንኮል ገብቶ በረከትህን ወሰደብህ” አለ።


ይስሐቅም ያዕቆብን ጠራው፥ ባረከውም፥ እንዲህ ብሎም አዘዘው፦ “ከከነዓናውያን ሴቶች ልጆች ሚስትን አታግባ፥


እኔ ባሰብሁ ቍጥር እደነግጣለሁ፥ ሰውነቴንም መንቀጥቀጥ ይይዘዋል።


“ስለዚህም ልቤ ተንቀጠቀጠ፥ ከስፍራውም ውጭ ዘለለ።


ልቤ በላዬ ተናወጠብኝ፥ የሞት ድንጋጤም ወደቀብኝ።


እነሆ፥ ለመባረክ ትእዛዝን ተቀብያለሁ፤ እርሱ ባርኮአል፥ ልመልሰው አልችልም።


ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድና ሊያጠፋ እንጂ ለሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወትን እንዲያገኙ፥ የተትረፈረፈ ሕይወትን እንዲያገኙ መጣሁ፤


እግዚአብሔር በጸጋው ስጦታና በመጥራቱ አይጸጸትምና።


በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ በሰማያዊ ስፍራ በክርስቶስ የባረከን፥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይባረክ።


ይስሐቅ ስለ መጪው ነገር ያዕቆብንና ዔሳውን በእምነት ባረካቸው።