Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢዮብ 37:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 “ስለዚህም ልቤ ተንቀጠቀጠ፥ ከስፍራውም ውጭ ዘለለ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 “ልቤ በዚህ በኀይል ይመታል፤ ከስፍራውም ዘለል ዘለል ይላል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 “በውሽንፍሩም ኀይል ልቤ ተንቀጠቀጠ፤ በፍርሃትም ተርበደበደ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 “ስለ​ዚ​ህም ልቤ ደነ​ገ​ጠ​ች​ብኝ፥ ከስ​ፍ​ራ​ዋም ተን​ቀ​ሳ​ቀ​ሰች።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ስለዚህም ልቤ ተንቀጠቀጠ፥ ከስፍራውም ተንቀሳቀሰ።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 37:1
15 Referencias Cruzadas  

እኔ ባሰብሁ ቍጥር እደነግጣለሁ፥ ሰውነቴንም መንቀጥቀጥ ይይዘዋል።


የነጐድጓድ ድምፅ ስለ እርሱ ይናገራል፥ እንስሶችም ደግሞ ስለሚመጣው ውሽንፍር ይጮኻሉ።”


የድምፁን መትመም ስሙ፥ ከአፉም የሚወጣውን ጉርምርምታ አድምጡ።


እግዚአብሔርም በዐውሎ ነፋስ ውስጥ ሆኖ ለኢዮብ መለሰ፤ እንዲህም አለ፦


ድንጋጤ ወደቀብኝ፥ እንዲሁም መንቀጥቀጥ አጥንቶቼን ሁሉ ተነዋወጡ።


ሥጋዬ አንተን ከመፍራት የተነሣ ደነገጠ፥ ከፍርድህ የተነሣ ፈርቻለሁ።


ጌታን በደመናት የሚተካከለው ማን ነው? ከአማልክትስ ልጆች ጌታን ማን ይመስለዋል?


እንዲህም ሆነ በሦስተኛው ቀን ማለዳ ነጎድጓድ፥ መብረቅና ከባድ ደመና እጅግም የበረታ የቀንደ መለከት ድምጽ በተራራው ላይ ሆነ፤ በሰፈሩ የነበሩት ሕዝብ ሁሉ ተንቀጠቀጡ።


በውኑ እኔን አትፈሩምን? ይላል ጌታ፤ ከፊቴስ አትደነግጡምን? አልፎት እንዳይሻገር አሸዋን በዘለዓለም ትእዛዝ ለባሕር ድንበር አድርጌአለሁ፤ ሞገዱም ቢናወጥ አያሸንፍም፥ ቢጮኽም አያልፈውም።


እኔ ሰምቻለሁ፥ አንጀቴ ራደብኝ፥ ከድምፁ የተነሣ ከንፈሮቼ ተንቀጠቀጡ፤ መበስበስ ወደ አጥንቶቼ ውስጥ ገባ፥ በውስጤም ተንቀጠቀጥሁ፥ በአስጨነቁን ሕዝብ ላይ እስኪመጣ ድረስ፥ የመከራን ቀን ዝም ብዬ እጠብቃለሁ።


ድንገትም የወኅኒው መሠረት እስኪናወጥ ድረስ ታላቅ የምድር መንቀጥቀጥ ሆነ፤ በዚያን ጊዜም ደጆቹ ሁሉ ተከፈቱ፤ የሁሉም እስራት ተፈታ።


መብራትም ለምኖ ወደ ውስጥ ሮጠ፤ እየተንቀጠቀጠም ከጳውሎስና ከሲላስ ፊት ተደፋ፤


ስለ ዳንም እንዲህ አለ፥ “ዳን የአንበሳ ደቦል ነው፥ ከባሳን ዘልሎ ይወጣል።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos