La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 27:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ይስሐቅም ልጁን፦ “ልጄ ሆይ፥ እንዴት ፈጥነህ አገኘኸው?” አለው። እርሱም፦ “ጌታ እግዚአብሔር ወደ እኔ ስለ አቀረበው ነው” አለ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ይሥሐቅ ልጁን፣ “ልጄ ሆይ፤ ከመቼው ቀንቶህ መጣህ?” ሲል ጠየቀው። ያዕቆብም፣ “እግዚአብሔር አምላክህ አሳካልኝ” ብሎ መለሰለት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ይስሐቅም “ልጄ ሆይ፥ እንዴት በቶሎ ልታገኝ ቻልክ?” አለው። ያዕቆብም “አምላክህ እግዚአብሔር ስለ ረዳኝ በቶሎ ለማግኘት ቻልኩ” አለው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ይስ​ሐ​ቅም ልጁን፥ “ልጄ ሆይ፥ ፈጥ​ነህ ያገ​ኘ​ኸው ይህ ምን​ድን ነው?” አለው። እር​ሱም፥ “አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፊቴ የሰ​ጠኝ ነው” አለ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ይስሐቅም ልጁን፦ ልጄ ሆይ እንዴት ፈጥነህ አገኘኸው? አለው እርሱም፦ እግዚአብሔር አምላክህ ወደ እኔ ስለ አቀረበው ነው አለ።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 27:20
4 Referencias Cruzadas  

እንዲህም አለ፦ “የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ እለምንሃለሁ፥ መንገዴን ዛሬ በፊቴ አቅናልኝ፥ ለጌታዬም ለአብርሃም ምሕረትን አድርግ።


ይስሐቅም ያዕቆብን፦ “ልጄ ሆይ፥ አንተ ልጄ ዔሳው እንደሆንህ ወይም እንዳልሆንህ እዳስስህ ዘንድ ቅረበኝ” አለው።


በውኑ ስለ እግዚአብሔር ሐሰትን ትናገራላችሁን? ስለ እርሱም ሽንገላን ታወራላችሁን?


“የጌታ የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ፤ ጌታ ስሙን በከንቱ የሚጠራውን ሳይቀጣው አያልፍም።