ዘፍጥረት 27:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ አባቱም ገብቶ፦ “አባቴ ሆይ” አለው እርሱም፦ “እነሆኝ፥ ልጄ ሆይ፥ አንተ ማን ነህ?” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያዕቆብም ወደ አባቱ ሄዶ፣ “አባቴ ሆይ” አለ፤ ይሥሐቅም፣ “እነሆ፤ አለሁ ልጄ፤ ለመሆኑ አንተ ማን ነህ?” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያዕቆብም ወደ አባቱ ሄደና “አባባ!” አለው፤ እርሱም “እነሆ፥ አለሁ! ለመሆኑ አንተ የትኛው ልጄ ነህ?” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ አባቱም አግብቶ፥ “አባቴ ሆይ፥” አለው፦ እርሱም፥ “እነሆኝ፤ ልጄ ሆይ፥ አንተ ማን ነህ?” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ አባቱም ገብቶ፦ አባቴ ሆይ አለው እርሱም፦ እነሆኝ፤ ልጄ ሆይ አንተ ማን ነህ? አለ። |
ያዕቆብም አባቱን አለው፦ “የበኩር ልጅህ እኔ ዔሳው ነኝ፥ እንዳዘዝኸኝ አደረግሁ፥ ነፍስህ ትባርከኝ ዘንድ ቀና በልና ተቀመጥ፥ ካደንሁትም ብላ።”
የዚያን ጊዜ ትጠራለህ ጌታም ይሰማሃል፤ ትጮኻለህ እርሱም፦ እነሆኝ ይላል። ከመካከልህ ቀንበርን ብታርቅ፥ በጣትህም መጠቆም ብትተው፥ ባታንጐራጉርም፥