Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 58:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 የዚያን ጊዜ ትጠራለህ ጌታም ይሰማሃል፤ ትጮኻለህ እርሱም፦ እነሆኝ ይላል። ከመካከልህ ቀንበርን ብታርቅ፥ በጣትህም መጠቆም ብትተው፥ ባታንጐራጉርም፥

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 የዚያን ጊዜ ትጣራለህ፤ እግዚአብሔርም ይመልስልሃል፤ ለርዳታ ትጮኻለህ፤ እርሱም፣ ‘አለሁልህ’ ይልሃል። “የጭቈና ቀንበር፣ የክፋትን ንግግርና ጣት መቀሰርን ከአንተ ብታርቅ፣

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ከዚያ በኋላ ትጸልያላችሁ፤ እኔም ጸሎታችሁን እሰማለሁ፤ የእርዳታ ጩኸት ትጮኻላችሁ፤ እኔም አለሁ እላችኋለሁ፤ እናንተ የጭቈናን ቀንበር ብታስወግዱ፥ የጣት ጥቆማንና የተንኰልን ንግግር ብታቆሙ፥

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ያን ጊዜ ትጠ​ራ​ለህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይሰ​ማ​ሃል፤ ትጮ​ኻ​ለህ፤ እር​ሱም፦ እነ​ሆኝ፥ ይል​ሃል። የዐ​መፅ እስ​ራ​ትን ከመ​ካ​ከ​ልህ ብታ​ርቅ፥ ጣት​ህ​ንም መጥ​ቀስ ማን​ጐ​ራ​ጐ​ር​ንም ብት​ተው፥

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 የዚያን ጊዜ ትጠራለህ እግዚአብሔርም ይሰማሃል፥ ትጮኻለህ እርሱም፦ እነሆኝ ይላል።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 58:9
31 Referencias Cruzadas  

በመከራ ቀን ጥራኝ፥ አድንህማለሁ አንተም ታከብረኛለህ።


እንዲህም ይሆናል፤ ሳይጠሩ እመልስላቸዋለሁ፥ ገናም ሲናገሩ እሰማለሁ።


ይጠራኛል እመልስለትማለሁ፥ በመከራውም ጊዜ ከእርሱ ጋራ እሆናለሁ፥ አድነዋለሁ አከብረውማለሁ።


እጆቻቸሁን ለጸሎት ወደ እኔ ስትዘረጉ፤ ዐይኖቼን ከእናንተ እሰውራለሁ፤ አብዝታችሁ ብትጸልዩም እንኳ አልሰማችሁም፤ እጆቻችሁ በደም ተበክለዋል፤


በዓይኑ ይጠቅሳል፥ በእግሩ ይናገራል፥ በጣቱ ያስተምራል፥


በተጨነቅሁ ጊዜ ጌታን ጠራሁት፥ መለሰልኝ፥ አሰፋልኝም።


አቤቱ፥ አድነኝ፥ ደግ ሰው አልቆአልና፥ ከሰው ልጆችም መተማመን ጐድሎአልና።


በጌታ ደስ ይበልህ፥ የልብህንም መሻት ይሰጥሃል።


እኔስ የመረጥሁት ጾም፥ የበደልን እስራት እንድትፈቱ፥ የቀንበርንስ ጠፍር እንድትለቁ፥ የተገፉትን አርነት እንድታወጡ፥ ቀንበሩን ሁሉ እንድትሰብሩ አይደለምን?


በማን ታላግጣላችሁ? በማንስ ላይ አፋችሁን ታላቅቃላችሁ? ምላሳችሁንስ በማን ላይ ታስረዝማላችሁ?


ተራፊም ትርጒም አልባ ነገር ተናግረዋል፥ ሟርተኞችም ሐሰተኛ ራእይ አይተዋል፤ የሚያሳስቱ ሕልሞችን ተናግረዋል፤ ባዶ ማጽናኛም ሰጥተዋል፤ ለዚህም ነው እረኛም ስለ ሌላቸው እንደ በጎች የተቅበዘበዙትና የተጨነቁት።


ወደ አባቱም ገብቶ፦ “አባቴ ሆይ” አለው እርሱም፦ “እነሆኝ፥ ልጄ ሆይ፥ አንተ ማን ነህ?” አለ።


ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከንቱ ነገርን ስለ ተናገራችሁ፥ ውሸተኛ ራእይንም ስላያችሁ፥ እነሆ እኔ በእናንተ ላይ ነኝ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


ዐምፀናል፥ ሐሰትን ተናግረናል፥ ጌታን ከመከተል ተመልሰናል፤ ግፍንና ዓመፅንም ተናግረናል፥ የኃጢአት ቃልንም ፀንሰን ከልብ አውጥተናል።


በኢየሩሳሌም ውስጥ በጽዮን የምትኖር ሕዝብ ሆይ፥ ከእንግዲህ ወዲህ አታለቅስም፤ በጩኸትም ድምፅ ይራራልሃል፥ በሰማህም ጊዜ ይመልስልሃል።


ወደ እርሱም ትጸልያለህ፥ እርሱም ይሰማሃል፥ ስእለትህንም ትሰጣለህ።


በማዳንህ ደስ ይለናል፥ በአምላካችን ስም ከፍ ከፍ እንላለን፥ ልመናህን ሁሉ ጌታ ይፈጽምልህ።


ጌታ በሚገኝበት ጊዜ ፈልጉት፥ ቀርቦም ሳለ ጥሩት፤


እነሆ፥ የጌታ እጅ ከማዳን አላጠረችም፥ ጆሮውም መስማት አልተሳናትም፤


አንድ ሦስተኛውን ክፍል ወደ እሳት አስገባለሁ፤ ብርም እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፤ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፤ እነርሱም ስሜን ይጠራሉ፥ እኔም እሰማቸዋለሁ፤ እኔም፦ “ይህ ሕዝቤ ነው” እላለሁ፥ እርሱም፦ “ጌታ አምላኬ ነው” ይላል።


ወይም በሐሰት የማለበትን ምንም ዓይነት ነገር ይመልስ፤ እርሱም የበደሉን መሥዋዕት በሚያቀርብበት ቀን በሙሉ የወሰደውን ነገር ይመልስ፥ በእርሱም ላይ አምስት እጅ ጨምሮበት ለባለቤቱ ይስጠው።


ጌታ ለሚጠሩት ሁሉ፥ በእውነት ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ ነው።


በጠራሁህ ቀን ቀርበህ፦ አትፍራ አልህ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios