La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 24:65 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሎሌውንም፦ “ሊገናኘን በሜዳ የሚመጣ ይህ ሰው ማን ነው?” አለችው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አገልጋዩንም፣ “ይህ ሊገናኘን በመስኩ ውስጥ ወደዚህ የሚመጣው ሰው ማን ነው?” ስትል ጠየቀችው። አገልጋዩም፣ “ጌታዬ ነው” ብሎ መለሰላት፤ እርሷም መሸፈኛዋን ተከናነበች።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“ያ በመስክ ውስጥ ወደ እኛ የሚመጣው ሰው ማን ነው?” ስትል የአብርሃምን አገልጋይ ጠየቀችው። አገልጋዩም “እርሱ ጌታዬ ነው” አላት። ስለዚህ በፍጥነት በሻሽ ፊትዋን ሸፈነች።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሎሌ​ው​ንም፥ “ሊቀ​በ​ለን በሜዳ የሚ​መጣ ይህ ሰው ማነው?” አለ​ችው። ሎሌ​ውም፥ “እርሱ ጌታዬ ነው” አላት፤ እር​ስ​ዋም ቀጸ​ላ​ዋን ወስዳ ተከ​ና​ነ​በች።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሎሌውንም፦ ሊገናኘን በሜዳ የሚመጣ ይህ ሰው ማን ነው? አለችው።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 24:65
9 Referencias Cruzadas  

ሣራንም አላት፦ እነሆ፥ ለወንድምሽ ሺህ ሚዛን ብር ሰጠሁት፥ ያም እነሆ ከአንቺ ጋር ባሉት ሁሉ ፊት የዐይኖች መሸፈኛ ይሁንሽ፥ ጽድቅሽ ለሰዎች ሁሉ ተገልጦአልና።”


ርብቃም ዐይኖችዋን አቀናች፥ ይስሐቅንም አየች፥ ከግመልም ወረደች።


ሎሌውም፦ “እርሱ ጌታዬ ነው” አላት፥ እርሷም መሸፈኛ ወስዳ ተከናነበች። ሎሌውም ያደረገውን ነገር ሁሉ ለይስሐቅ ነገረው።


የመበለትነት ልብሷን አውልቃ፥ ማንነቷ እንዳይታወቅ ፊቷን በሻሽ ተከናንባ ወደ ተምና በሚወስደው መንገድ ዳር ባለች ኤናይም በተባለች ከተማ መግቢያ ላይ ተቀመጠች፤ ይህን ያደረገችው፥ ሴሎም ለአካለ መጠን ቢደርስም፥ እርሷን እንዲያገባ አባቱ አለመፈለጉን ስላወቀች ነው።


መስታወቱን፤ ከጥሩ በፍታ የተሠራውን ልብስ፤ የራስ ጌጡን፤ ዐይነ ርግቡን ሁሉ ይነጥቃቸዋል።


ወፍጮ ወስደሽ ዱቄትን ፍጪ፤ መሸፈኛሽን አውጪ ረጅሙንም ልብስሽን አውልቀሽ ጣይው፤ ባትሽን ግለጪ፥ ወንዙን ተሻገሪ።


በዚህ ምክንያት፥ በመላእክትም ምክንያት ሴት በራስዋ ሥልጣን ሊኖራት ይገባል።


እንዲሁም ደግሞ ሴቶች ከትሕትናና ራስን ከመግዛት ጋር በሚገባ ልብስ ራሳቸውን ያስጊጡ፤ ይሁንና በቄንጠኛ የጸጉር አሠራር ወይም በወርቅ ወይም በዕንቁ ወይም ዋጋው እጅግ በከበረ ልብስ አይሁን።